Tender Detail

Tender Details

  • Company በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ጦርሀይሎች ወደ 18 በሚወስደው መንገድ 700ሜ ገባ ብሎ ኪዳኔ ጉበሬ ህንፃ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 -3713324
  • Website
  • Deadline09 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-09 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Cleaning And Janitorial Equipment , Materials , Stationery Materials

በልደታ ክ/ከተማ የወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት በአስተዳደሩ ስር ለሚገኙ ተቋማት መጠቀሚያ ሎት1፡-የደንብ ልብስ፣ ሎት 2፡ -የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት 3፡-የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት4፡ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ ሎት 5፡-የደንብ ልብስ ስፌት እና ሎት 6፡-የመኪና ወንበር ልብስና የቶዮታ ደብል ጋቢና ፒካፕ መኪና ኬሪቦይ /TOYOTA HILUX CARRYBOY DOUBLE CAB/ በግልጽ

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 003/2018

 

በልደታ ክ/ከተማ የወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት በአስተዳደሩ ስር ለሚገኙ ተቋማት መጠቀሚያ ሎት1፡-የደንብ ልብስ፣ ሎት 2፡ -የፅህፈት መሳሪያ፣ ሎት 3፡-የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት4፡ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ ሎት 5፡-የደንብ ልብስ ስፌት እና ሎት 6፡-የመኪና ወንበር ልብስና የቶዮታ ደብል ጋቢና ፒካፕ መኪና ኬሪቦይ /TOYOTA HILUX CARRYBOY DOUBLE CAB/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ስለሚፈልግ የጨረታው መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

ስለዚህ፡-

1.     ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ለሎት 1፡ 15,000 ብር፣ ለሎት 2፡ 7,000 ብር፣ ለሎት 3፡ 5,000 ብር፣ ለሎት 4፡ 8,000 ብር፣ ለሎት 5፡ 3,000 ብር እና ለሎት 6፡ 6,000 ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል።

2.     ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት እንዲሁም በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3.     ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ በመክፈል ከል/ክ/ከ/ወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።

4.     ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5.     ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው እቃዎች በእያንዳንዱ ነጠላ ዋጋ ላይ ቫት ጨምረው መሙላት ይጠበቅባቸዋል።

6.     የጨረታው አሸናፊ ውል ከተፈፀመበት ቀን ጀምሮ እቃውን በራሱ ትራንስፖርት በሰጠው ናሙና መሰረት ንብረት ክፍል ማስረከብ ይኖርበታል።

7.     ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግም ሆነ ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

8.     ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት በተወዳደሩባቸው ሎቶች ላይ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9.     የጨረታው አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ15 /በአስራ አምስት/ ቀን ውስጥ የውል ስምምነት ባሸነፈበት ጠቅላላ ብር ላይ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርበታል።

10. የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን ንብረት ውል በገባ በ15 ቀን ውስጥ ማቅረብ ይኖርበታል።

11. በአንድ ዕቃ ላይ ሁለት የተለያየ ዋጋ ማቅረብ ከጨረታው ያሰርዛል።

12. የጨረታ ሳጥኑ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰአት ታሽጎ በዕለቱ በ4፡30 ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ታሸጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወ/2/ፋ/ጽ/ቤት 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ይከፈታል።

13. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።

14. ወረዳው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ፡- ጦር ሀይሎች ወደ 18 በሚወስደው መንገድ ሆላንድ ኤምባሲ ፊት ለፊት አባ ጅፋር መስጂድ አጠገብ ል/ክ/ከተማ ወረዳ 2 አስተዳደር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ስልክ ቁጥር 011-3-69-21-41 በልደታ ክ/ከተማ የወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

በልደታ ክ/ከተማ የወረዳ 2 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender