Tender Detail

Tender Details

  • Company ዝግባ የሕፃናትና አረጋውያን መርጃ የበጎ አድራጎት ድርጅት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 12 05 69 99
  • Website
  • Deadline07 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-07 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing

ዝግባ የሕፃናትና አረጋውያን መርጃ የበጎ አድራጎት ድርጅት የ2017/2018 (እ.ኤ.አ የ2025) በጀት ዓመት የነበረውን የሂሳብ እንቅስቃሴ በጨረታ አወዳድሮ ለማስመርመር ይፈልጋል።

ዝግባ የሕፃናትና አረጋውያን መርጃ የበጎ አድራጎት ድርጅት


በድጋሚ የወጣ የሂሳብ ምርመራ /ኦዲት ሥራ/ ጨረታ ማስታወቂያ

 

ዝግባ የሕፃናትና አረጋውያን መርጃ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከ3,254 በላይ ለከፋ ችግር የተጋለጡ ሕፃናት ጧሪ ያጡ አረጋውያንና በዝቅተኛ የነሮ ደረጃ ለሚገኙ ችግረኛ ሴቶች በአዲስ አበባ፣ በባሕር ዳር እና እንጅባራ ከተማ የድጋፍና እንከብካቤ አገልግሎት እየሰጠ ያለ ማኅበረሰብ እቀፍ ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው።

ስለሆነም ድርጅቱ የ2017/2018 (እ.ኤ.አ የ2025) በጀት ዓመት የነበረውን የሂሳብ እንቅስቃሴ በጨረታ አወዳድሮ ለማስመርመር ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

1.     በሂሳብ ምርመራ ሥራ ተሰማርተው የሚሠሩ፣

2.     በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና ሌሎች አስፈላጊና ሕጋዊ መረጃዎች ያሏቸው፡፡

3.     ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ዋጋ በፖስታ በማሸግ ባሕር ዳር ግሸ አባይ ክ/ከተማ ቀበሌ 02 ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

4.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበትን ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

5.     ከአሁን በፊት ምርመራ ካደረጉባቸው መ/ቤቶች የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

6.     ጨረታው ክፍት ሆኖ የሚቆየው ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ በ10፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል።

7.     ጨረታው የሚከፈተው በእለቱ ጨረታው ባለቀበት ቀን በ10፡30 ይሆናል፡፡

8.     በተጨማሪም አስፈላጊ መረጃዎችን ከጨረታ ማስገቢያ ቀን በፊት ቢሮ ድረስ በመቅረብ መመልከት ይቻላል።

9.     ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 የጨረታ ሰነድ በመግዛት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤

 

ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ:- በ09 12 05 69 99/

09 84 29 29 29 ይደውሉ፡፡

 

ዝግባ የሕፃናትና አረጋውያን መርጃ የበጎ አድራጎት ድርጅት

Save Tender