የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ግዥ ቡድን የተለያዩ ግዥዎችን በተቋሙ ተጠቃሚ ለሆኑ ዲፓርትመንቶች የእቃና አገልግሎት ግዥዎችን በ8 ምድብ ከፍሎ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2018
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ግዥ ቡድን የተለያዩ ግዥዎችን በተቋሙ ተጠቃሚ ለሆኑ ዲፓርትመንቶች የእቃና አገልግሎት ግዥዎችን በ8 ምድብ ከፍሎ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ሎት 1 የጽህፈት እቃ
ሎት 2 ህትመት
ሎት 3 ፈርኒቸር እና ቋሚ ዕቃ
ሎት4 መድሃኒት እና የህክምና ዕቃ
ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
ሎት 6. የፓርቲሽን እና ሌሎች የጥገና ስራ
1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ፣ ቲን ሰርተፍኬት ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴርወይም ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትንየምስክር ወረቀት እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. የጨረታ ሰነዱ በኤንቨሎፕ ታሽጎ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻው በፖስታታሽጎ የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 64 ማስገባት ይኖርበታል፡፡
4. ጨረታ አሸናፊ ተጫራች የውል ማስከበሪያ ካሸነፈባቸው ከእቃው ዋጋ 10% cpo በባንክ የተረጋገጠ ማስያዝ አለባቸው፡፡
5. ጨረታው እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ተዘግቶ በ4፡30 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች በጋዜጣው ላይ በተገለጹት የጨረታ ዓይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች በዝዙት ጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ ገጽ ላይ በመፈረም ማቅረብና ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
8. የጨረታ ማስከበሪያ ከሎት 3 እስከ 6 ለእያንዳንዱ ሎት 10,000 (አሥር ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 1 እና 2 5000 (አምስት ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ CPOበኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ስም ተሰርቶ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
9. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የጨረታ ዓይነቶች ውስጥ የተዘተዘሩትን ያንዱ ዋጋ እና የጠቅላላውን ዋጋ በግልጽ ከተቋሙ ገዝተው በወሰዱት ሰነድ ላይ ማስፈርይኖርባቸዋል፡፡ተጫራቾች ሎት 01 በተገለፁት ጨረታ ዓይነቶች ናሙና ማቅረብ የግዴታ ሲሆን ነገር ግን ከባድ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ቋሚ እቃዎች ላይየምትወዳደሩ ተጫራቾች ከሰነዱ ጋር ካታሎግ ማስገባት ይኖርበታል፣ሌሎቹ በጨረታ ሰነዱ በተገፀው ስፔስፊኬሽን መሰረት ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
10. በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች በሙሉ መወዳደር የምትችሉት ባመረታችሁት እቃ ብቻ ሲሆን አምራች መሆናችሁን የሚገልፅ ደብዳቤ በአደራጃችሁ ፅ/ቤት ሃላፊ የተፈረመ ደብዳቤ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዛችሁ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
11. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ኮ/ቀራኒዮ ከተማ ካራ ቆሬ ወደ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን መውጫ
ወረዳ 02ጤና ጣቢያ በሚገኘው የጤና ጣቢያው ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 64
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ
