የሀዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ት/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች፣ አልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች የተለያዩ ዓይነት ጫማዎች የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች የቤትና ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 27/2018
በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ
የሀዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ት/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች፣ አልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች የተለያዩ ዓይነት ጫማዎች የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች የቤትና ቢሮ ዕቃዎች የመኪና እና የሞተር ሳይከል አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች(ግለሰብም ሆነ ድርጅት) ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደስ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00፣ ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ-6፡00 ሰዓት ድረስ በቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደርቡድን በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተው ቀጥታ አካውንት (1000174515488) የማይመለስ ብር 100( አንድ መቶ ብር) በማስገባት hawassaawegaged (ECCH-ዕቃ አወጋገድ ሥራ ሂደት 2018) በሚለው የቴሌግራም ግሩፕ ስሊፕ በመላክ የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላከሎት ማድረግ ይቻላል፡፡
3. ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እና ያገለገሉ ሞተርሳይከሎች ላይ መወዳደር የሚፈልግ ተጫራች ማንኛውም እድሜው ከከ8 አመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ መወዳደር ይችላል፡፡
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም የተዘጋጀ የሚረቱበትን ጠቅላለ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለት CPO በማሰራት የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል በተጨማሪ ሀራጅ ጨረታ ለሚሳተፉ ተጫራቾች ላገለገሉ ተሽከርካሪዎች ለእያንዳንዳቸው ብር 1,000,000(አንድ ሚሊዮን ብር) የጨረታ ዋስትና (CPO) ለእያንዳንዱ የጨረታ ኮድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
5. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው) ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው (በስድስተኛው) ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡05 ፔፕሲ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የሐዋሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት አዲሱ መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ተከፍቶ ጨረታው የሚጀምር ሲሆን ግልፅ ጨረታው ከተጠናቀቀ ከ10 ደቂቃ በኋላ የሀራጅ ጨረታው ይጀመራል። ነገር ግን ጨረታው በዓል እሁድ ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታ ይሆናል፡፡
6.ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠውው ከፍት ቦታ ከነ ቫቱ በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልከ በመሙላት በታሸገ ኤንቬሎፕ ወይም ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከዚህ ሰነድ ውጭ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ ቅ/ጽ/ ቤቱ ለመቀበል አይገደድም፡፡
7 ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም ፡፡ በተጨማሪ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋ እና መግለጫ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሃደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም፡፡ በጨረታው ለሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ክሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል፡፡
10.ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ሳያዩ ለሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
11. ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው፡፡
12. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5(አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሚ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል፡፡
13. ቅ/ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር 046-212-53-96/ 046-212-65-95
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት
