በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2018 በጀት ዓመት የአላቂና ሌሎች የቢሮ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ካራት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2018 በጀት ዓመት የአላቂና ሌሎች የቢሮ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል ፡፡ በዚህ መሠረት በጨረታ ለመወዳደር ለምትፈልጉ ተጫራቾች/ድርጅቶች መሟላት ያለባቸው፡-
1. በአላቂና ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፤
2. በዘርፉ የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወርቀት ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፤
3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት /TIN NO/ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፤
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑ፤
5. በዘርፉ የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፤
6. በዘርፉ መልካም የሥራ አፈፃፀም ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
7. ተጫራቾች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአላቂና ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ዝርዝር የጨረታ ሠነድ /ስፔስፊኬሽን/ የያዘ የጨረታ ሠነድ ይህ የጨረታ ሠነድ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 18 በመቅረብ ሠነዱን በ300 ብር መግዛት ይችላሉ፡፡
8. ዕጩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ዋስትና ከታወቀ ባንከ የሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ ወይም በጥሬ ገንዘብ /10,000 ብር /አሥር ሺህ ብር/ ብቻ በእናት ፖስታ ውስጥ አሽገው ለኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብሎ በአድራሻ በመፃፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
9. ዕጩ ተጫራቾች የጨረታው የቴከኒካል ግምገማና የፋይናንሻል ግምገማ ሂደት የሚካሄደው በመደበኛ የጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጠው እና በማስታወቂያው ላይ በተገለጹት ዝቅተኛ የተፈላጊ መስፈርቶች /Minimum Riquirement/ መሠረት ይሆናል፡፡
10. ዕጩ ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ በአንድ ኤንቨሎፕ ፖስታ የሚቀርብ ሆኖ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሠነዶችን እያዳንዳቸው አንድ አንድ ኦርጅናልና አንድ አንድ ኮፒ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ጋር በትክክል በታሽገ በአንድ ኤንቨሎፕ /በአንድ እናት ፖስታ/ ውስጥ በማስገባት በማሽግ ማህተም በማሳረፍ አድራሻ በመግለጽና በመፈረም ሆኖ ጨረታው የሚታሸገው በ16ኛው የሥራ ቀን ልክ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
11. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋን ማቅረብ አይቻልም ፡፡
12. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን የውል ማስከበሪያ ሰነድ 20% በማስያዝ ባሸነፉበት የአላቂና ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች የውል ማስከበሪያ ይዘው ቀርበው በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ ውል ባይገባ በዘርፉ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
13. ተጫራቾች ጨረታው ይከፈታል በተባለው በ16ኛው ቀን በመንግሥት የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ፡፡
14. የተጫራቾች ተሟልተው ያለመገኘት የጨረታው አከፋፈት ሥነ-ሥርዓት ሊያስተጓጉል አይችልም።
15. ፍ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
16. ፍ/ቤቱ አስቀድሞ የዋጋ ጥናት ያደረገ በመሆኑ ተጋንኖ የሚቀርቡ ዋጋዎች ከወዲሁ ጨረታውን ውድቅ ሊያደርግ ይችላል፡፡
ለበለጠ መረጃ: 0912083959/0467730929/0946550214/
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ካራት
