የሰ/ምስ/ሪጅን ኢትዮ ቴሌኮም ከአገልግሎት የተመለሱ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ የተለያዩ አይነቶች ያገለገሉ ወንበሮች፣ የተለያዩ የእንጨት ምሰሶዎች፣ ያገለገሉ መጋረጃዎች፣ የብረት በርሜሎች ከአገልግሎት የተበላሹ ካዝናዎች፣ አሮጌ ጀኔሬተር፣ የማያገለግሉ ሶላር ፓኔሎች፣ ከአገልግሎት የተመለሱ ቆርቆሮዎች እና ሌሎች የመሳሰሉት ዕቃዎች ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ኢትዮ ቴሌኮም
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ቴሌኮም የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ከአገልግሎት የተመለሱ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ የተለያዩ አይነቶች ያገለገሉ ወንበሮች፣ የተለያዩ የእንጨት ምሰሶዎች፣ ያገለገሉ መጋረጃዎች፣ የብረት በርሜሎች ከአገልግሎት የተበላሹ ካዝናዎች፣ አሮጌ ጀኔሬተር፣ የማያገለግሉ ሶላር ፓኔሎች፣ ከአገልግሎት የተመለሱ ቆርቆሮዎች እና ሌሎች የመሳሰሉት ዕቃዎች ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/2018
ጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት ቀን የካቲት 06 ቀን 2018 ዓ.ም
ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የካቲት 25 ቀን 2018 ዓ.ም
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም
በኢትዮ ቴሌኮም የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ከአገልግሎት የተመለሱ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ የተለያዩ አይነቶች፣ ያገለገሉ ወንበሮች፣ የተለያዩ የእንጨት ምሰሶዎች፣ ያገለገሉ መጋረጃዎች፣ የብረት በርሜሎች፣ ያገለገሉ ካዝናዎች፣ ጀኔሬተር በርሜሎች፣ ሶላር ፓኔሎች፣ ቆርቆሮዎች እና ሌሎች ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ ለብረታ ብረት ፋብሪካዎች ቅድሚያ በመስጠት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከየካቲት 06 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ የካቲት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ደሴ/ፒያሳ በሚገኘው የኢትዮ ቴሌኮም ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 202 የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል እና በመግዛት መወዳደር የምትችሉ ሲሆን ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትፈልጉ ተጫራቾች ደሴ/መላኩ አካባቢ በሚገኘው ዋናው ዕቃ ግ/ቤት ቢሮ በመገኘት መጠየቅ ይቻላል፤ እንዲሁም ንብረቶቹን መመልከት ለሚፈልጉ ደሴ ካራጉቱ በሚገኘው ዕቃ ግምጃ ቤት የታደሰ መታወቂያችሁን እና የጨረታ ሰነዱን የገዛችሁበትን ደረሰኝ በመያዝ መጎብኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደሴ/ፒያሳ በሚገኘው ዋናው ጽ/ቤት የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
ኩባንያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሰ/ምስ/ሪጅን ኢትዮ ቴሌኮም (ደሴ)
