Tender Detail

Tender Details


በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስተዳዳር የቦሌ 17 ጤና ጣቢያ ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስተዳደር የቦሌ 17 ጤና ጣቢያ


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/2018

 

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስተዳዳር የቦሌ 17 ጤና ጣቢያ ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

ሎት

የግዥው አይነት

የጨረታ ቁጥር

የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን

1

ሎት 1

አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ

02/2018

2,500.00

2

ሎት 2

የጽዳት ዕቃዎች

 

8,700.00

3

ሎት 3

የህትመት ስራዎች

 

10,500.00

4

ሎት 4

የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

 

15,000.00

5

ሎት 5

የደንብ ልብስ

 

8,300.00

6

ሎት 6

ቋሚ ዕቃዎች

 

8,000.00

7

ሎት 7

የህክምና ዕቃዎች

 

20,000.00

8

ሎት 8

የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች

 

10,000.00

 

በመንግስት ግዥና ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1.     ተጫራቾች በጨረታው ለመክፈል በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውንና ቫት ከፋይ የሆነ TIN Number ማቅረብ የሚችሉና በአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ QR-Code ደረሰኝ ያለው መሆን አለበት።

2.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር በየሎቱ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ አለባቸው።

3.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 የማይመለስ ብር 200.00 /ብር ሁለት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ሰነድን በግዥ ክፍል መግዛት ይችላሉ።

4.     ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ና ማንዋሉን በታሸገ ፖስታ በ2 ኮፒ በማድረግ ከ2፡30 -11፡00 ሰዓት ለዚህ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።

5.     ዋጋ ማቅረቢያው ላይ በእያንዳንዱ ገጽ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

6.     ፎቶ ኮፒውን በአንድ ፖስታ፣ ዋናውን በአንድ ፖስታ ተደርጎ ፖስታው ላይ ዋና ወይም ፎቶ ኮፒ ተብሎ ይገለጽ።

7.     ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጐ በዛኑ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን 11ኛው ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ማለትም ሰኞ ይከፈታል።

8.     ከወጣው ጨረታ ብዛት ላይ መ/ቤት 20 በመቶ የመጨመር 20 በመቶ የመቀነስ መብት አለው።

9.     ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው። አሸናፊ ተጫራቾች ባመጣው ናሙና መሰረት ዕቃውን ማቅረብ ይጠበቅበታል። ቋሚ ዕቃዎችን መ/ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ ይኖርበታል።

10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. ተጫራቾች የሚወዳዳሩበት በቀረበው ሎት መሰረት ፖስታ ላይ መገለጽ ይኖርበታል።

12. ተጫራቾች ለአሸነፉበት ዕቃ ዋጋ 10% CPO ማስያዝ አለባቸው።

13. በራሳቸው ትራንስፖርት የጨረታ አሸናፊ ድርጅት መ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

14. በማስታወቂያው ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።

15. ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች የንግድ ፍቃዳችሁን ዋናውንና ኮፒ ሰነድ ልትገዙ ስትሉ ማቅረብ አለባቸሁ፡፡

16. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋውን መሙላት ያለባቸው በተሸጠላቸው ሰንድ ላይ ብቻ እና እያንዳንዱ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።

አድራሻ፡- ከኢምፔሪያል 100 ሜትር ገባ ብሎ ሳሚ ህንፃ ፊት ለፊት ኬቢ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ጀርባ መሆኑን እንገልጻለን። ቢሮ ስልክ .ቁ 011 8 22 99 52

 

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አስተዳደር የቦሌ 17 ጤና ጣቢያ

Save Tender