በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት የግዥ ቡድን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ለ 2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የህዝብ ትራንስፖርት እና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥዎችን ከዚህ በታች የተጠቀሱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት
በድጋሚ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 11/2018
በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት የግዥ ቡድን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ለ 2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የህዝብ ትራንስፖርት እና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥዎችን ከዚህ በታች የተጠቀሱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1. የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ
ሎት 2 የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ የስራ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፡ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /tin no/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ያላቸው።
2. ተጫራቾች ከግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ, የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
3. ለሚወዳደሩባቸው የአገልግሎት አይነቶች የጨረታ ማስከበሪያ ከጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
4. የጨረታው ሰነድ አቀራረብ 1 ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል 1 ቴክኒካል ሰነድ ኮፒ፡ 1 ፋይናንሽያል ሰነድ ኦሪጅናል እና የፋይናንሽያል ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም 1 ሲፒኦ ለብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ መቅረብ አለበት።
5. የጨረታ ሰነዱን እስጢፋኖስ ላይ በሚገኘው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አዲሱ ሕንፃ 9ኛ ፎቅ የዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 400.00 በአካውንት ቁጥር 1000001455285 (ቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት) በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
6. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንድ ቀን ብሎ በመቁጠር 11ኛው ቀን ላይ ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በተመሳሳይ ቀን ከጥዋቱ 4፡30 ላይ ጨረታው ይከፈታል።
7. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ እንደ ማሳሰቢያ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- እስጢፋኖስ ከሚገኘው ከማሪዎት ሆቴል ፊት ለፊት የቂርቆስ ክ/ከ/አስ/አዲሱ ሕንፃ 9ኛ ፎቅ
ስልክ፡- 0115 54 82 64 / 0118-69-43-66
በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት
