አዲስ ምዕራፍ በጎ አድራጎት ማህበር በ2025 የስራ ዘመን ሶስት ኘሮጀክቶችን የፈፀመ ሲሆን እነዚህን ኘሮጀክቶች ማለትም በአጠቃላይ 5 /አምስት/ ፎልደሮችን የታደሰ የሙያ ፈቃድ ባለው ድርጅት የኦዲት ሪፖርት ማሰራት ይፈልጋል።
አዲስ ምዕራፍ በጎ አድራጎት ማህበር ለጤናና ለልማት
የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ ምዕራፍ በጎ አድራጎት ማህበር ለጤናና ለልማት/New Chapter Charitable Association for Health & Development/ በ1997 ዓ/ም ቫይረሱ በደማቸው ባለባቸው አባላት የተመሰረተና ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን በኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አስተዳደር ሙሉ እውቅና ያለው እና በ2011 ዓ/ም በዳግም ምዝገባው በመዝገብ ቁጥር 2907 የተመዘገበ ድርጅት ነው፡፡ የማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት በደ/ብርሃን አጼ ምኒልክ ክፍለ ከተማ ሰላም ጮራ ቀበሌ የደ/ብርሃን ጤና መምሪያ ግቢ ውስጥ ይገኛል። ማህበሩ በ2025 የስራ ዘመን ሶስት ኘሮጀክቶችን የፈፀመ ሲሆን እነዚህን ኘሮጀክቶች ማለትም በአጠቃላይ 5 /አምስት/ ፎልደሮችን የታደሰ የሙያ ፈቃድ ባለው ድርጅት የኦዲት ሪፖርት ማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም የዘመኑን ግብር የከፈለ፣ የቫት ተጠቃሚ የሆነ፣ የታደሰ የኦዲት ሙያ ፈቃድ ያለው፣ እንዲሁም ሌሎች ህጋዊ ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችል የኦዲት ስራ ድርጅት ማመልከትና መወዳደር ይችላል። የማመልከቻ ጊዜ ገደብ ጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በማህበሩ ዋና መ/ቤት በአካል በመገኘት ማመልከት ትችላላችሁ። ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ግልጽ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- ስ.ቁ 0913 21 38 15 / 0912 76 08 86
Email: yohiminalu@gmail.com
አዲስ ምዕራፍ በጎ አድራጎት ማህበር ለጤናና ለልማት
