Tender Detail

Tender Details


በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 02 17/20 ጤ/ጣቢያ ከዚህ በታች በዝርዝር የተቀመጡትን ነገሮች በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 02 17/20 ጤና ጣቢያ


3ኛ ዙር የጨረታ አስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 003/18

 

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የ17/20 ጤና ጣቢያ፡-

ሎት ቁጥር /የሎት ዝርዝር የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮ ብር

ሎት 1. ቋሚ እቃ ... ብር 5,000

ሎት 2. የተለያዩ ህትመቶችን … ብር 2,000

ሎት 3. አላቂ የጽዳት እቃ … ብር 5,000

ሎት 4. ቋሚ የህክምና እቃ … ብር 10,000

በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል። ስለዚህ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1.     ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2.     በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገበ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3.     የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው።

4.     ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

5.     ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው።

6.     የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 57 እየቀረቡ መግዛት ይቻላል። ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በቢሮ ቁጥር 56 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

7.     ጨረታው በ10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

8.     ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።

9.     ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።

10. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት ቢሮ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

11. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- ቦሌ ሩዋንዳ ጃፓን ኤንባሲ ገባ ብሎ ወረዳ 02 አጠገብ ይገኛል።

ስልክ ቁጥር፡- 011-6-68-72-98

 

በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 02 17/20 ጤ/ጣቢያ

Save Tender