የሲዳማ ብሔ/ክል/መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ ቋሚና አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎችን በብሔራዊ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሲዳማ ብሔ/ክልል መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ሲዳማ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔ/ክል/መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ ቋሚና አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችና የጽዳት ዕቃዎችን በብሔራዊ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ኮሚሽኑ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልጋቸው ቋሚና አላቂ ዕቃዎች ዝርዝር - የግዥ ጨረታ ቁጥር 03
▪ የተለያዩ የቢሮ የጽህፈት መሳሪያዎች
▪ የተለያዩ የቢሮ የፅዳት አላቂ ዕቃዎች
1) በሚወዳደሩበት መስክ የ2018 ዓ/ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ፤ የግብር ከፋይነት ማስረጃ ያላቸው ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ፤ ከመንግስት ዕዳ ነፃ ስለመሆናቸውና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ::
2) ማንኛውም ተጫራች በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠየቀውን ህጋዊ ማስረጃዎች ለጨረታ ከሚያቀርበው ዋጋ ጋር ዋናውንና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3) ተጫራቾች በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ እንደፍላጎታቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000 00 ሺህ ብር የያዘ ሲፒኦ/ CPO/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ፤ እንዲሁም ጥሬ ገንዘብ በማያያዝ ከዋናው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው:
4) ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ከሞሉ በኋላ የጨረታውን ሠነድ አንድ ኦርጂናል እና አንድ ፎቶ ኮፒ ሰነድ በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው እንደገና በአንድ ትልቅ ኤንቬሎፕ ውስጥ አስገብተው በኤንቨሎፑ ላይ የተጫራቾች ድርጅት ማህተም አርፎበት በሰም ታሽጎ ፖስታው እስከ አስራ አንደኛው ቀን 8፡oo ሰዓት ድረስ ወደ ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ::
5) በዚሁ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት በኮሚሽኑ ግዥና ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 12 ይከፈታል::
6) ተጫራች በጨረታው ዕለት ናሙና በዝርዝር በጽሑፍ እና የድርጅቱ ማህተም አርፎበት የግድ ማቅረብ አለበት ናሙና ለማያቀርብ ተጫራች የሚያቀርበው ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም ::
7) ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታውን ሰነድ በኢትዮጵያ ብር /200/ ሁለት መቶ ብር በመክፈል ከግዥና ንብረት አስ/ር ስራ ሂደት መግዛት ይችላሉ::
8) የሚቀርበው የዕቃ ዝርዝርና ብዛት በሚሸጠው የጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ ስለሆነ ተወዳዳሪዎች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ መመሪያውን በሚገባ በማንበብ መወዳደርይኖርባቸዋል:: የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር ማብራሪያ የያዘ ስለሆነ ይበልጥ ተቀባይነት ይኖረዋል ::
9) የጨረታው አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነታቸው ከተገለፀ ጊዜ ጀምሮ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መግባት ይኖርባቸዋል፡፡ ውል የማይገቡ ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ይወረስባቸዋል፡፡
10) ኮሚሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው ::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-2127-875 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡ የሲዳማ
የሲዳማ ብሔ/ክ/መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን
