የአሰላ መምህራን ት/ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለኮሌጁ አገልግሎት የሚውሉ ቋም ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የአሰላ መምህራን ት/ኮሌጅ
ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 1
የአሰላ መምህራን ት/ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለኮሌጁ አገልግሎት የሚውሉ ቋም ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም -
1. ለተጠየቁት እቃዎች የታደሱ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆናችሁ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላችሁ እና በፌዴራል ፣በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክርወረቀት ያላችሁ ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚትችሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኮሌጁ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በመቅረብ ሰነዱን 500.00/አምስት መቶ/ ብር በንክገቢ በማድረግ በግዥ መውሰድ ትችላለቹ፡፡
2. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመከፈላቸው እና ጨረታ ላይ
ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በተከታታይ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ጠዋት 3:00 ሰዓት ማቅረብ እና ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ጠዋት በ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኮሌጁ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
4.ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንከ በከፍያ ማዘዣ(C.P.O.) ለኤሌከትሮኒከስ እና ጽህፈት መሳሪያዎች ለእያንዳንዳቸው 50 000.00/ሃምሳ ሺህ/ ብር ለመኪና ጎማዎች እና ፅዳት እቃዎች 20,000.00(ሃያ ሺህ ብር) በኮሌጁ ስም በማስያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. አሸናፊው ተጫራች አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ከምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ አሰላ ከተማ በሚገኘው በኮሌጁ ግቢ ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
6. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0930107417/0911742980 ይጠይቁ፡፡
የአሰላ መምህራን ት/ኮሌጅ
