በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማለትም የደንብ ልብስ 2. የኤልከትሮኒከስ 3. የህዝብ ትራንስፖርት 4. የህትመት ውጤቶች በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት
የግልፅ ጨረታ ግዥ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 002/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማለትም የደንብ ልብስ 2. የኤልከትሮኒከስ 3. የህዝብ ትራንስፖርት 4. የህትመት ውጤቶች በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ፍቃድ ያላችው እና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. የአቅራቢነትን ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
4. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በፖስታ ማቅረብ የሚችል ለሎቶች የተቀመጠው በኢትዮጵያ ብር
1. ሎት 1 ደንብ ልብስ 5000
2. ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ 10000
3. ሎት 3. የህዝብ ትራንስፖርት 400
4. ሎት 4 የህትመት ውጤቶች 500
5. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ በተቋሙ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7 በአካል እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን የጨረታ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ̈ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
7. ጨረታው በ10ኛው ቀን 11፡30 ታሽጎ በማግስቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
8. ተጫራቾች ያሸነፉበትን የውል ማስከበሪያ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል ።
9. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው መቅረብ የማይችሉትን ቋሚ እቃዎች በ/ቤቱ ባቀረበው ናሙና መሰረት በአካል ማሳየት የግዴታ ነው።
10. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ እና ውል በተሰጣቸው 5 ቀን ውስጥ በራሳቸው ትራንስፖርት ለፅ/ቤቱ ማስረከብ አለበት።
11. መ/ቤቱ ጨረታ ሰነድ ላይ ካቀረበው እቃ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡
አድራሻ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ገርጅ ናይጀሪያ ኢንባሲ አፖርትመንት አጠገብ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ወይም ገርጅ ፖሊስ ጣቢያ ጀርባ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0118 721 213
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ፋይናንስ ጽ/ቤት
