የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት የግዥ ቡድን በ2018 በጀት ዓመት ግልጽ ጨረታ ሎት 1 ስቴሽነሪ፣ ሎት 2 የደንብ ልብስ ግዥ፣ ሎት 3 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 4 የህትመት ውጤቶች፣ ሎት 5 የፕሪንተር የኮምፒውተር የፎቶ ኮፒ ጥገና ከነመለወዋጫው፣ ሎት 6 የፕሪንተር ቀለም ግዥ በሁለተኛ ዙር በጨረታ አወዳድሮ መገጸም ይፈልጋል።
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት 002/2018
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ሁለተኛ ዙር ግዥ በ2018 በጀት ዓመት ግልጽ ጨረታ ሎት 1 ስቴሽነሪ፣ ሎት2 የደንብ ልብስ ግዥ፣ ሎት 3 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 4 የህትመት ውጤቶች፣ ሎት 5 የፕሪንተር የኮምፒውተር የፎቶ ኮፒ ጥገና ከነመለወዋጫው፣ ሎት 6 የፕሪንተር ቀለም ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት እንድትጫረቱ ይጋብዛል፣
1. ተጫራቾች በሚሳተፉበት የግዥ አይነት በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀትና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ናሙና እንዲያቀርቡ የተጠየቁባቸውን እቃዎች ሰነዳቸውን ሲያገቡ አብረው የሚወዳደሩበትን ናሙና የማስገባት ግዴታ አለባቸው፤
4. የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው የገቢ ግብር ባለስልጣን ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 ብር 10,000፣ ሎት 2 ብር 5,000፣ ሎት 3 ብር 5,000፣ ሎት 4 ብር 5,000፣ ሎት 5 ብር 5,000፣ ሎት 6 ብር 5,000 የካ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በየሎቱ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፤
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱነ በሚገባ በመሙላት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ፋይናሺያል ዶክመንት እና ቴክኒካል ሰነድ ለየብቻ ቴክኒካል ሰነድ ለብቻ የተሞላበት ዋጋ ለብቻ ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያየ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ዋና እና ኮፒ መሆኑን በመግለጽ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ ተጫራቾች ጨረታውን ሲያሸነፉ የውል ማስከበሪያ 10 ፐርሰንት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. የጨረታ ሰነድ እስከ 10 ቀን ብቻ ተሸጦ የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ እለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የመንግስት ግዥ ቡድን ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።
9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበትና ቫትን ያካተተ መሆኑና አለመሆኑ ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ቫትን እንዳካተት ተደርጐ ይወስዳል።
10. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያላሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ∶- መገናኛ ማራቶን ሕንፃ ፊት ለፊት በሚገኘው የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደርህንፃ 4ኛ ፎቅ ስልክ 0118107894
የየካ ክፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት
