በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የሚከተሉትን እቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከሰኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት 002/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ
ፅ/ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የሚከተሉትን እቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
- ሎት አንድ:- አላቂ እና ቋሚ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት ሁለት:- የደንብ ልብስ እና የጽዳት ዕቃ
- ሎት ሦስት:- የህትመት ስራዎች
* ሎት አራት ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
*ሎት አምስት የመኪና ማስዋቢያ እቃዎች
*ሎት ስድስት፡-የተለያዩ ኮምፒዉተር ፣ፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ማሽን ጥገና እንዲሁም የጥገና መለዋወጫ ዕቃዎች
* ሎት ሰባት ፡- የኤሌክትሪከ የቢሮ እቃዎች ጥገና እና የጥገና መለዋዋጫ ዕቃዎች
*ሎት ስምንት ፡-አጠቃላይ የቢሮ ፅዳት አገልግሎት ግዥ
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል::
1. ከሚወዳደሩበት ዕቃ ወይንም አገልግሎት ግዥ ጋር ለመወዳደር ተያያዥነት ያለዉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃዎችን (ከሊራንስ) ከግብርአስገቢው መ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ::
2. በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት ግዥ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
3. ለተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
4. የአገር ውስጥ የድጋፍ አቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት (በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት) የተደራጁ መሆኑን እና ከአደራጃቸዉ አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ለአጠቃላይ ከሎት አንድ እስከ ሎት አስር 0.5% ለእያንዳንዳቸዉ ሎቶች በባንከ በተመሰከረለት (C.P.O) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ C.P.O መሰራት ያለበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለአዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከለኛ ግብር ከፋዮችቅርንጫፍ ፅ/ቤት በሚል አድራሻ መሆን አለበት፡፡
5. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መክፈቻው ቀን ድረስ ሳሊተ ምህረት ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት ሜሪዲያን ህንፃ ከሚገኘው የአዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ከግዥ ቡድን ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ:: የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያጠቃለለ እና ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናልና ኮፒውን ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባችሁ::
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጥንቃቄ በማሸግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይገባቸዋል:: ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት በመ/ቤቱ አዳራሽ 2ተኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ይከፈታል:: እያንዳንዱ ተጫራች ለጨረታ ለመወዳደር በሚቀርብበት ወቅት ፋይናንስ እና ቴከኒካል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ የዋጋ ማቅረቢያ /ዝርዝር/ በተለያየ ፖስታ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ኮፒ እና ኦርጅናል ተለይቶ በፖስታዉ ዉጫዊ ገጽ መጻፍ አለበት፡፡
7. ሰነዱን በሚመልስበት ወቅት ስልጣን ባለው አካል መፈረምና የድርጅቱ ማህተም መደረግ አለበት ነገር ግን የሚፈርመው አካል ተወካይ ከሆነ የውክልና ማስረጃ መያያዝ አለበት፡፡
8. አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም::
9. የጨረታው አሸናፊ የአሸናፊነት ደብዳቤ እንደደረሰዉ የዉሉን ዋጋ 10% (አስር ፐርሰንት) C.P.O በውል ማስከበሪያነት በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል::
10.ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም ዕቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ ናሙናዎችንም ለንብረት አስተዳደር ከፍል ማስረከብ አለባቸው::
ኪየጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታዉ ከተከፈተበት ጀምሮ ለ90 ቀናት መቆየት አለበት፡፡
12.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 01116731504
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከስኛ
ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፍ ፅ/ቤት /አዲስ አበባ/
