የሰላም ፍሩትስ ማህበር እንደ ኤሮፓውያን አቆጣጠር የ 2025 ሂሳብ በተመሰከረላቸው ኦዲተሮች ማስመርመር ይፈልጋል።
ሰላም ፍሩትስ
የኦዲት ስራ ጨረታ ማስታወቂያ
ሰላም ፍሩትስ በማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መዝገብ ቁጥር 5945 የተቋቋመ ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ማህበር ነው።ሰላም ፍሩትስ ማህበር በሰላም ሕፃናት መንደር አድገው በተለያዩ የስራ መስክና ኃላፊነት በተሰማሩ ልጆች የተቋቋመ የበጎ አድራጎት ማህበር ሲሆን፣ ዓላማውም ከህፃናት ማሳደጊያ ወጥተው ወደ ማህበረሰቡ ሲቀላቀሉ የተለያዩ ችግሮች የገጠማቸውን ልጆችን ከገጠማቸው ግዚያዊ ችግሮች ተላቀው ኑሯቸውን በተገቢው መልኩ መምራት ይችሉ ዘንድ ድጋፍ ማድረግ ነው።
የሰላም ፍሩትስ ማህበር እንደ ኤሮፓውያን አቆጣጠር የ 2025 ሂሳብ በተመሰከረላቸው ኦዲተሮች ማስመርመር ይፈልጋል።
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡-
➢ የታደሰ ንግድ ፍቃድ
➢ የታደሰ ንግድ ምዝገባ
➢ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የሙያ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያላቸው። ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8 የስራ ቀናት ውስጥ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
አድራሻ፡- የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ኮተቤ ሃና ማሪያም ቤተክርስቲያን ገባ ብሎ ሰላም ህፃናት መንደር ጊቢ ውስጥ
ሰላም ፍሩትስ
