Tender Detail

Tender Details

  • Company በአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሰሜን ጤና ጣቢያ
  • Address አራዳ ከፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ስሙ ሰሜን መዘጋጃ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0118-12-68-04
  • Website
  • Deadline10 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price150.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-10 00:00:00
  • Categories Stationery Materials , Used Items

በአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሰሜን ጤና ጣቢያ ያገለገሉ ንብረቶችን፣ ወረቀቶችን እና ካርዶችን በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሰሜን ጤና ጣቢያ


ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 04/2018

 

በአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሰሜን ጤና ጣቢያ ያገለገሉ ንብረቶችን፣ ወረቀቶችን እና ካርዶችን በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

1.     ንብረቶቹን በጤና ጣቢያው በመገኘት ማየት እና የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 150.00 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

2.     ለየምድቦቹ (ሎቶች) የተቀመጠውን የጨረታ ማስከበሪያ በካሽ ወይም በCPO ማስያዝ አለባቸው፡፡

3.     ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ በዋጋ መሙያው ሰንጠረዥ ላይ በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡

4.     የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ዋጋ ከፍለው ንብረቶቹን በ3 ቀናት ውስጥ ማንሳት አለባቸው፡፡

5.     ለጨረታው አሸናፊዎች ካሸነፉበት ንብረት ዋጋ ላይ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ተቀናሽ ይደረግላቸዋል። በጨረታው ለሚሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ይመለስላቸዋል፡፡

6.     የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ7ኛው የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡

7.     ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ፡- አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ

ስልክ ቁጥር 0111-12-94-72

 

በአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የሰሜን ጤና ጣቢያ

 

Save Tender