የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Addis Ababa City Admin. Landholding Registration and Information Agency (በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር LHR/A/NCD/002/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የሚገዛው ዕቃ ተዛማጅ አገልግሎት
• ሎት 1፡- የሰራተኛ ዩኒፎርም /Employee uniform/
• ሎት 2፡- የሰራተኛ ጫማ
• ሎት 3፡- የህትመት አገልግሎት ግዥ
በመሆኑም በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ እና በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ሎት1. 300,000.00 /ሶስት መቶ ሺህ ብር ብቻ/፣ ሎት 2. 190,000.00 /አንድ መቶ ዘጠና ሺህ ብር ብቻ/፣ ሎት3. 5,000.00/ አምስት ሺህ ብር ብቻ/
3. በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ /CPO/ ወይም ቢድ ቦንድ በመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ስም አሰርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታውን ፋይናንስ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም ቴክኒክ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን ትክክለኛውን ቅጅ ለየብቻው በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ናሙና እንዲቀርብ ለተጠየቁት እቃዎች ከጨረታው መክፈቻ ቀን ቀደም አድርገው ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከተጠቀሰው ቀን ዘግይቶ የሚቀርብ ናሙና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
6. የደንብ ልብስ እና ጫማ የሚጫረቱ ተጫራቾች ናሙና ማቅረብ እና ስፔስፊኬሽን በተጠየቀበት መሰረት ማቅረብ ግዴታ ነው፡፡
7. የጨረታው ፋይናንስ ሰነድ የሚከፈተው እና ግምገማ የሚካሄደው ከላይ ከተራ ቁጥር 1-6 የተመለከቱት ቴክኒካል መረጃዎች እና የእቃው ናሙናዎች በትክክል ተሟልቶ መቅረባቸው ሲረጋገጥ ነው።
8. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
9. በጨረታው አሸናፊው ድርጅት የአሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ የኤጀንሲው የዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለበት፡፡
10. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
11. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 6፡30 እና ከቀኑ 7፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ከጎላጎል ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ለም ሆቴል አካባቢ የመሬት ይዞታ ምዝገባ መረጃ ኤጀንሲ ዋናው መስሪያ ቤት 13ኛ ፎቅ ላይ የኤጀንሲው የመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት በመምጣት የማይመለስ 300 ብር /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
12. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚያው እለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
13. ኤጀንሲው አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
14. ኤጀንሲው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከጎላጎል ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ዋናው መስሪያ ቤት 13ኛ ፎቅ ወይም በስልክ ቁጥር 0118125085 ደውለው ያነጋግሩ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ
