በጎንደር ከተማ አስተዳደር የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት አገልግሎት የሚሰጣቸው የጽህፈት መሣሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በጎንደር ከተማ አስተዳደር የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በጎንደር ከተማ አስተዳደር የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት አገልግሎት የሚሰጣቸው የጽህፈት መሣሪያ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-
• በሎት 1፡- የጽህፈት መሳሪያ
• በሎት 2፡- የፅዳት እቃዎች
• በሎት 3፡- የኤሌክትሪክ እቃዎች
ማቅረብ የሚጠበቅባችሁ መረጃ፡-
1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ፈቃድ ያለው፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው።
3. የሚገዛው እቃ የገንዘብ መጠኑ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋጋጥ የምስክርወርቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ከሎት 1 እስከ ሎት 3 የቀረቡትን እቃዎች ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔሲፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ብር የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስገባት አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል በጎንደር ከተማ አስተዳደር የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ግዥና ፉይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይቻላል።
8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሀሳባቸውን አንድ ወጥ በመሆኑ ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ አራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ግዥ ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ስዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት በጎንደር ከተማ አራዳ ከፍለ ከተማ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 12 በመምጣት የጨረታ ሰንድ መግዛት ይችላሉ። ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
10. ተጫራቾች ዋጋውን በሚሞሉበት ወቅት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመጫረቻ ሰነድ በፖስታ የታሸገ ሆኖ ኦርጅናል ስም፣ ፊርማ ማህተም መኖር አለበት።
12. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርብ ቅሬታ ካለ ጨረታው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የሥራ ቀን ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን፤ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ የሚቀርብ ቅሬታ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን።
13. ለተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ አራዳ ክፍለ ከተማ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 12 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር፡- 0582119640 ደውሎ መጠየቅ ይችላል፡፡
14. ዕቃውን በሚፈልግበት ወቅት በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ የሚችል።
15. ተጫራቾች መጫረት/መወዳደር የሚችሉት የንግድ ዘርፍ በሚመለከታቸው ይሆናል።
16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- አሸናፊው ተጫራች የሚቀርበው እቃ ኦርጅናልና በወጣው ስፔሲፊኬሽን መሰረት ይሆናል።
– የሚፈፀመው ግዥ ከበጀት አንጻር ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል።
– አሸናፊው የሚለየው በእያንዳንዱ ሎት ጠቅላላ ዋጋ ይሆናል፡፡
ከተዘረዘሩት እቃዎች ውስጥ አንዱን ያልሞላ ከውድድር ውጪ ይሆናል።
በጎንደር ከተማ አስተዳደር የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
