ኢኽላስ የልማትና ተራድኦ ድርጅት የ2017 ዓ.ም የፋይናንስ ሂሳቡን በውጭ ኦዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል።
Ikhlas Development and Relief Association (ኢኽላስ የልማትና ተራድኦ ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የኦዲት አገልግሎት የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የኢኽላስ የልማትና ተራድኦ ድርጅት (Ikhlas Development and Relief Organization)
ኢኽላስ የልማትና ተራድኦ ድርጅት በመዝገብ ቁጥር 7106 በኢፌድሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አገር በቀል ድርጅት ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን በተለያዩ የልማትና የተራድኦ ስራዎች እየተሳተፈ ይገኛል። ስለሆነም የድርጅታችን የ2017 ዓ.ም የፋይናንስ ሂሳቡን በውጭ ኦዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል። በመሆኑም በዘርፉ የተሰማራችሁና የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ የኦዲት ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-
1. የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ (AABE) ያወጣው የታደሰ የሙያ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
3. በበጎ አድራጎት ድርጅቶች የኦዲት ምርመራ ላይ በቂ የሥራ ልምድ ያላቸው። የመወዳደሪያ ሰነድ አቀራረብ፡-
4. ተጫራቾች የኦዲት አገልግሎት ዋጋችሁን (በቫት ጨምሮ) እና ሥራውን አጠናቃችሁ የምታስረክቡበትን ጊዜ የሚገልጽ የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
5. ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ወሎ ሰፈር HMM ህንፃ ቢ/ቁ 303 ለድርጅቱ አስተዳደር ክፍል መቅረብ ይኖርበታል።
ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር፡- 0911706137/0913999925 አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ወሎ ሰፈር HMM ህንፃ ቢ/ቁ 303
ኢኽላስ የልማትና ተራድኦ ድርጅት
