የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፤ ሞተር ሳይክሎች፤ ጎማዎች፤ ለመለዋወጫ አገልግሎት ብቻ የሚውል የሞተር ሳይክል፤ የባጃጅ እና የብስክሌት አካል ባሉበት ሁኔታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት
የጨረታ ማስታወቂያ
የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ሲጠቀምባቸው የነበሩ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፤ ሞተር ሳይክሎች፤ ጎማዎች፤ ለመለዋወጫ አገልግሎት ብቻ የሚውል የሞተር ሳይክል፤ የባጃጅ እና የብስክሌት አካል ባሉበት ሁኔታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ተሽከርካሪዎቹ እና ንብረቶቹ ካሳንቺስ ኢሲኤ (ECA) ጀርባ ባለው መ/ቤታችን ይገኛሉ።
1. ማንኛውም ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን እና በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጧቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማየት ይቻላል።
2. ተጫራቾች የንብረቱ መነሻ ዋጋ 25% በባንክ በተረጋገጠ አዲስ አበባ በሚገኙ ቅርንጫፍ ባንኮች ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
3. ጨረታው የካቲት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
4. አሸናፊው ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለአገልግሎት መ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛሉ።
5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር- 011 126 14 70 ወይም 011 126 10 38
ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት
