በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ/ንብ/አስ/ቡድን በ2018 በጀት አመት በወረዳው ላሉ ሴ/መ/ቤቶች ለስራ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. ፕላንት ማሽነሪ /ኤሌከትሮኒክስ/ ፣ ሎት 2 የውሃ እቃ፣ ሎት 3 የግንባታ እቃ፣ ሎት 4 አሸዋና ጠጠር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የባሶና ወራና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 9/2018
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ/ንብ/አስ/ቡድን በ2018 በጀት አመት በወረዳው ላሉ ሴ/መ/ቤቶች ለስራ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. ፕላንት ማሽነሪ /ኤሌከትሮኒክስ/ ፣ ሎት 2 የውሃ እቃ፣ ሎት 3 የግንባታ እቃ፣ ሎት 4 አሸዋና ጠጠር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተመለከቱትን መሰፈርቶች የሚያሟሉ እና በየንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ሆነው መጫረት የሚፈልጉ የንግድ ድርጅቶች
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)ያላቸው፤
4. የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያለው፤
5. የግዥ መጠኑ ከብር 200, 000/ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፍይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
6. የእቃው አይነት ዝርዝር መገለጫ ወይም እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ ። የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በሞ/ጅ/ወ/ገ/ጽ/ቤት የፋይናስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 115 ገንዘቡን በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 001 መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
7. ተጫራቾች በምትጫረቱበት ሎት ላይ የጨረታ ማስከበሪያ ፕላንት ማሽነሪ/ኤሌክትሮኒክስ/ 60000 /ስልሳ ሺህ ብር/ብቻ፣ የውሃ እቃ 20000 /ሃያ ሺህ ብር/ብቻ፣ የግንባታ እቃ 50000 /ሀምሳ ሺህ ብር/ ብቻ እና አሸዋና ጠጠር 10000 /አስርሺህ ብር/ ብቻ በጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ ወይም ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
8. ተጫራቾች የሚሰጡትን የጨረታ ዋጋ የጨረታ ሰነዱ በሚጠይቀው መሰረት በማዘጋጀትና በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30/ሶስት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ/ ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት በግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 001 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ጨረታውም በዚሁ ቀን 3፡31/ሶስት ሰአት ከሰላሳ አንድ ደቂቃ/ ተዘግቶ 4፡00/አራት ሰአት/ ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 001 ውስጥ ይከፈታል፡፡
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
10. ጨረታ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ብሄራዊ በአል ላይ የሚውል _ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል ::
11. በጨረታው ተሳታፊዎች ፖስታ ላይም ሆነ ዋጋ መሙያው ላይ ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ወይም ህጋዊ ፊርማችሁን ማስቀመጥ ይኖርባችኋል።n
12. በጨረታው ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ መሞላት አለበት፣ ሆኖም ግን ስርዝ ድልዝ ካለ ስለመስተካከሉ ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
13. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በጠቅላላው ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላ ይሆናል።
14. መ/ቤቱ እቃዎችን 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል። ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች በተቋሙ በአካል በመምጣት በማየት መሙላት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።አሸናፊዉም ድርጅት ያሸነፈውን እቃ ወረዳው ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
15. ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ትግባራዊ የሚደረግ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 0116880408 ወይም 0116880330 ላይ መደወል ይችላል።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ/ንብ/አስ/ቡድን
