Tender Detail

Tender Details


በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የእድገት ጮራ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ዕድገት ጮራ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የእድገት ጮራ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች

•         ሎት 1 የደንብ ልብስ ግዥ

•         ሎት 2 ለአላቂ የቢሮ እቃዎች

•         ሎት 3 ለህትመት

•         ሎት 4 አላቂ የህክምና እቃ

•         ሎት 5 ለአላቂ የት/ት እቃዎች

•         ሎት 6 አላቂ የጽዳት ዕቃ

•         ሎት 7 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች

•         ሎት8 የቋሚ ኤሌክትሪክ ጥገና

•         ሎት 9 አገልግሎት

•         ሎት 10 ለህንጻ ቁሳቁስ ተገጣጣሚ እቃ ጥገና

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።  ሰለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳደሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1.       የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርብ።

2.       የገቢዎችእና ጉምሩክ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።

3.       ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ቫት/ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4.       የአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር ማያያዝ የሚችሉ መሆን አለበት።

5.       ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ በአንድ ሎት 100/ አንድ መቶ ብር/ በመከፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ዕድገት ጮራ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

6.       የጨረታ ማሰከበሪያ ሁሉም ሎቶች በአንድ ላይ 20,000 ሂያ ሺ በባንክ በተረጋገጠ  C.P.O ብቻ ማስያዝ አለበት።

7.       የመወዳደሪያ ዋጋው ከነቫት በማስቀመጥ በግልጽ ተጠቅሶ መጻፍ ይኖርበታል። የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ዋናውንና ኮፒ ለየ ብቻ በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የሚወዳደሩበት ዕቃናሙና /specification/ ማቅረብ አለባቸው። አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከታወቀ በኃላ በ15 ቀናት ውስጥ ከት/ቤቱ ጋር ውል መዋዋል አለበት፡፡ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ደረጃውን የጠበቀ ዕቃዎችን ትዕዛዙ በደረሳቸው በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ በናሙናው መሰረት አጠናቀው ለት/ቤቱ ንብረት ክፍል ሲያስረክቡና በጥራት ኮሜቴ ተፈትሾ ሲያልፍና በተቋሙ ኃላፊ ገቢ እንዲሆን ከታዘዘ በኃላ ይከፍላቸዋል።

8.       የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 የጨረታው ሳጥን ይታሸግና በዛው እለት በ4፡30 ሰዓት ዕደገት ጮራ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋ/ግ/ንብ/አሥ የቡድን መሪ ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

9.       የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% c.p.0 ብቻ በቅድሚያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

10.   መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11.   ከጥር 1 ጀምሮ የገቢዎች የወጣው ህግ ተግባራዊ ማዲረግ አለበት።

አድራሻ ፡- ከአያት አደባባይ ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ ገመናዬ ማርያም ቤ/ክ መግቢያ ላይ ይገኛል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011 639 1334/ 011 893 1407

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስሚኩራ ክ/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ዕድገት ጮራ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

Save Tender