ድርጅታችን ላቪ ኢን ላይፍ ኢትዮጵያ (Love in Love Ethiopia) እ.ኤ.አ የ2025 በጀት ዓመት ሂሳብ በውጭ ኦዲተር አወዳድረን ለማስመርመር ለማሰራት ይፈልጋል።
ላቪ ኢን ላይፍ ኢትዮጵያ
የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ላቪ ኢን ላይፍ ኢትዮጵያ (Love in Love Ethiopia) በምዝገባ ቁጥር 2556 በኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በሀገር አቀፍ ደረጃ ተመዝግቦ በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በህፃናት፣ በወጣቶችና በሴቶች ዙሪያ የተለያዩ የልማትና የማህበረሰብ አቀፍ ሥራዎችን እየሰራ ያለ ሀገር በቀል NGO ነው።
በመሆኑም የድርጅቱን እ.ኤ.አ የ2025 በጀት ዓመት ሂሳብ በውጭ ኦዲተር አወዳድረን ለማስመርመር ለማሰራት ስለምንፈልግ ከዚህ በታች በተገለጸው መሰረት ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ እንዲወጣልን እንጠይቃለን፡፡
በዚህም መሰረት-
1ኛ/ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ በዘርፉ የታደሰ የሙያ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ እና በዘርፉ የተሻለ ልምድ ያለው የማይመለስ ፎቶ ኪፒ፡፡
2ኛ/ ተጫራቾች ለሥራው የሚያስፈልገውን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
3ኛ/ ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስር (10) የሥራ ቀናት ውስጥ በሀዋሳ ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመቅረብ የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ሁለት መቶ ብር (200.00) ብቻ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
4ኛ/ ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ በሰም በታሸገ ፖስታ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5ኛ/ ጨረታው የሚዘጋው በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት በሚገኘው የአስ/ር እና ፋይናንስ የስራ ክፍል በዕለቱ ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
አድራሻ፡- ሀዋሳ ከተማ፣ ፒያሳ፣ ከቀድሞ ኢትዮ ቴሌኮም ዋና መ/ቤት በስተጀርባ፤
ስልክ +251 462201438
ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ከተገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ላቪ ኢን ላይፍ ኢትዮጵያ
