በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ እና በስሩ ለሚገኙ ለ12ቱ ፖሊስ ጣቢያዎች በ2018 ዓ/ ም በጀት አመት የሚያስፈልጋቸውን ሎት 1 የፅህፈት እቃዎች፣ ሎት 2 የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የጭነት መኪና አይሱዙ፣ ሎት 4 የጥገና እቃዎች፣ ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ናቸው ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ እና በስሩ ለሚገኙ ለ12ቱ ፖሊስ ጣቢያዎች በ2018 ዓ/ ም በጀት አመት የሚያስፈልጋቸውን ሎት 1 የፅህፈት እቃዎች፣ ሎት 2 የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የጭነት መኪና አይሱዙ፣ ሎት 4 የጥገና እቃዎች፣ ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ናቸው ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት።
1. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ሆነው በስራ መስኩ የተሰማሩ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በመንግስት ግ/ን አስ ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ለሎት1 5,000 /አምስት ሺህ/ ብር ሲፒአ በመ/ቤታችን ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
3. በሎት የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በን/ስ/ላ/ክ ፖሊስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 503 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቸላሉ፡፡ ተጫራቾች በጨረታው በአዲስ ዘመን ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት በጨረታው ለመወዳደር
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በን/ስ/ላ/ክ/ከ ፖሊስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 503 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ጨረታውን ሲወዳደሩ በእያንዳንዱ ከላይ በተ.ቁ ላይ የተጠቀሱትን ሰነዶች አሟልቶና እያይዞ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት ይኖርበታል።
5. ጨረታው በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በክ/ከተማው የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ዕቃ ላይ መ/ቤቱ መመዘኛ መስፈርት /Specification/ ባወጣንባቸው ዕቃዎች ላይ ሌላ የራስን መመዘኛ /Spect/ አውጥቶ መወዳደር አይቻልም፡፡
7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
8. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበ በጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚ መ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
10. የጨረታው አሸናፊ ለውል ማስከበሪያ 10% ዋስትና መስጠት ይኖርበታል፡፡
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉበሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ
ን/ስ/ላ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ በስልክ ቁጥር 0114423315/0114431529 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የን/ስ/ላ/ክ/ከ/ፖሊስ መምሪያ
