የደቡብ ኦሞ ሰብል አብቃይ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን በደቡብ ኦሞ ዞን እና በአሪ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች ላሉ አርሶ አደሮች በያዝነው 2017 ዓ.ም በበልግና መኸር የአፈር ማዳበሪያ /NPS ዓ.ም በበልግና መኸር የአፈር ማዳበሪያ /NPS NPSB እና UREA በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።
የደቡብ ኦሞ ሰብል አብቃይ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ጂንካ
የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ
የደቡብ ኦሞ ሰብል አብቃይ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን በደቡብ ኦሞ ዞን እና በአሪ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች ላሉ አርሶ አደሮች በያዝነው 2017 ዓ.ም በበልግና መኸር የአፈር ማዳበሪያ /NPS ዓ.ም በበልግና መኸር የአፈር ማዳበሪያ /NPS NPSB እና UREA በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።
ስለሆነም
ተጫራቾች ከድርጅቱ የማራገፈያ ጣቢያዎችን ዝርዝር መግለጫ በመውሰድ ለማጓጓዝ የሚፈለገውን የማድረሻ ዋጋ በጠጠርና በአስፋልት መንገድ በአማካይ በኩንታል በአንድ ኪሎ ሜትር ተሰልቶ በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-
1) በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር ከፍሎ የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰ እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፣
2) ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ መንግስታዊ አካል የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
3) ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የሥራ ዘርፍ ተሰማርቶ ሥራውን በሚገባ ስለመወጣቱ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል፣
4) የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲያመች በአንድ ወረዳ ውስጥ በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይችሉም፣
5) ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብር 300,000/ሦስት መቶ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
6) በጨረታ አሸናፊ የሚሆን ማንኛውም ድርጅት ውል ከመፈፀሙ በፊት ያሸነፈበትን ጭነት የማጓጓዣ ዋጋ 10% በቅድሚያ ያስይዛል፣
7) ተጫራቾች የተሽከርካርዎች ዝርዝር ቢያንስ 2,000/ሁለትሺህ/ ኩንታል በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችሉ መኪኖችን /የሰሌዳ ቁጥር፣ የመኪና ዓይነትና የመጫን አቅም/ የሚያስረዳ ፈቃድ ከሰጠው መንግስታዊ አካል የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
8) የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች ግዴታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 800 /ስምንት መቶ ብር/ በመክፈል ከደቡብ ኦሞ ሰብል አብቃይ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ዋና ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላል።
9) የጨረታውን ሰነዶች በኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይችላል።
10) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ ህጋዊ ወኪሎቻቸው 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋት 3፡00 ሰዓት የጨረታ ተሳታፊዎች በተገኙበት በዩኒየኑ ዋና ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሁኔታ ይከፈታል።
11) ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በመከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ጂንካ ከተማ-አርክሻ ኮንፊደንስ አካዳሚ ት/ቤት ጎን
ስ. ቁጥር፡- 0913 362 884 ፣ 0916 855 525
የደቡብ ኦሞ ሰብል አብቃይ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን
ጂንካ
