በጉለሌ ክ/ከተማ ስፖርት ምክር ቤት ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ ማስፈፀሚያ የሚውሉ የስፖርት ትጥቅ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በጉለሌ ክ/ከተማ ስፖርት ምክር ቤት ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ግዥ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡ 001/2018/ ዓ.ም
በጉለሌ ክ/ከተማ ስፖርት ምክር ቤት ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ ማስፈፀሚያ የሚውሉ የስፖርት ትጥቅ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1. የስፖርት ትጥቅ ለማቅረብ በዚህ የስራ ዘርፍ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች፡፡
1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤
3. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፣
5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 1 30,000.00 ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
6. ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀው ዝርዝር ጉዳዮችና የተጫራቾችን መመሪያ የያዘ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመግዛት 9ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ፣ IN ONE 59
7. ጨረታው መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀን ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ግዥ ቡድን በቢሮ ቁጥር 02 ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው የሚታሸግበት በ10ኛው ቀን 11፡30 ይሆናል።
8. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ግዥ ቡድን በቢሮ ቁጥር 02 ይከፈታል።
9. የምትወዳደሩባቸውን የደንብ ልብሶች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
10. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል። ህጋዊ ወኪል ለመሆናቸው የሚገልጽ ማስረጃ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሣስባለን፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ካልተገኙ ጨረታውን ለመከፈት የማያስተጓጉል መሆኑን እናሣውቃለን፡፡
11. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
12. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው እና በእያንዳንዱ ላይ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ማህተም ያላደረገ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፣
13. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሠረት የሞሉትን ዋጋ /VAT/ ያካተተ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መጥቀስ ይኖርበታል። ካልተጠቀሰ እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፣
14. ኦርጅናል እና ኮፒውን ሰነድ ለየብቻ አድርጎ በማያያዝ ማስገባት ይኖርበታል፣
15. በጨረታው ላይ የእቃውን ብዛት 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይቻላል።
16. በውሉ ላይ 25% መጨመር ይቻላል፡፡
17. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡-
አድራሻ፡- አዲሱ ገበያ ኖክ ጀርባ የጉ/ክ/ከተማ አዲሱ ህንጻ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 04
በስልክ ቁጥር፡- 0913687313 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በጉለሌ ክ/ከተማ ስፖርት ምክር ቤት ጽ/ቤት
