የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ግብርና መምሪያ የግብርና ግብዓት አቅርቦትና የገጠር ፋይናንስ ቡድን ለ2018/2019 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል 60,420 /ስልሳ ሺህ አራት መቶ ሃያ/ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ሰቆጣ ከተማ ባለው ዋቢ ዩንየን ማዕከላዊ መጋዝን በማንሳት በብ/አስ/ሩ በሚገኙ ወረዳዎች 20 ሃያ መሠረታዊ ማኅበራት መጋዘን ድረስ ለማጓጓዘ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርት ድርጅቶች በግል
የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ግብርና መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ዐ04/2018
የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ግብርና መምሪያ የግብርና ግብዓት አቅርቦትና የገጠር ፋይናንስ ቡድን ለ2018/2019 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል 60,420 /ስልሳ ሺህ አራት መቶ ሃያ/ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ሰቆጣ ከተማ ባለው ዋቢ ዩንየን ማዕከላዊ መጋዝን በማንሳት በብ/አስ/ሩ በሚገኙ ወረዳዎች 20 ሃያ መሠረታዊ ማኅበራት መጋዘን ድረስ ለማጓጓዘ ብቃት ያላቸውን የትራንስፖርት ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች።
1. ከሚመለከተው የመንግሥት ተቋም የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድና የዘመኑ የመንግሥት ግብር ስለመክፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረበ ግዴታ መሆኑ፣
2. የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት /ቲን/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
3. በጨረታው የሚሣተፉ ተጫራቾች ከ70 ኩንታል በላይ የመጫን አቅም ያለው እና በዘመኑ የታደሰ ምዝገባ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ 1 እስከ 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
5. የሚጓጓዘውን የአፈር ማዳበሪያ አይነት መጠን ርቀት በኪሎ ሜትር ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በዋግ ኸምራ ብ/አስ/ዞን በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 3 ማግኘት ይቻላል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታዎች ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በሚወዳደሩበት በዋቢ ዩንየን ስም ማስያዝ አለባቸው።
8. ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በአንድ ፖስታ በማሸግ በዋግ ኸምራ ግብርና መምሪያ የግብርና ግብዓት አቅ/የግ/ፋ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል። በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ጀምሮ የጨረታ ኮሚቴዎች ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የግብርና መምሪያ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የጨረታ ሰነዱ ይከፈታል፣
9. መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ውሉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ግብርና መምሪያ
