በሲዳማ ብ/ክ/መ የሥራ ክህሎት ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ የማጆ ቲቭት (TVET) ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት የሥልጠና ዕቃዎች፣ ሞተር ሳይክሎች እንዲሁም ማሽነሪዎችና ሌሎች ቋሚና አላቂ ዕቃዎችንና ስቴሽነሪ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በዘርፉ ህጋዊ የሆኑ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የማጆ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
በሲዳማ ብ/ክ/መ የሥራ ክህሎት ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ የማጆ ቲቭት (TVET) ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት የሥልጠና ዕቃዎች፣ ሞተር ሳይክሎች እንዲሁም ማሽነሪዎችና ሌሎች ቋሚና አላቂ ዕቃዎችንና ስቴሽነሪ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በዘርፉ ህጋዊ የሆኑ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ TIN number ያላችሁ፣ የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) መመዝገባችሁን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ያላችሁ በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያገኛችሁ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች ከማጆ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/ሥ/ሂደት ቢሮ በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 400 (አራት መቶ) ብር ብቻ በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 /አስራ አምስት/ በሥራ ቀናት ውስጥ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት በመጫረቻ ሰነድ ላይ የሚሞሉት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን በግልጽ በመፃፍ በጥንቃቄ ድልዝ ሰረዝ ሳይኖርበት በመሙላት የድርጅቱን ከብ ማህተም በማኖር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በፖስታው በማሸግ ኦርጅናሉንና ኮፒውን ለይቶ በመጻፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዕውቅና ካለው ባንክ የCPO ገንዘብ 10,000 (አስር ሺህ) ብር ብቻ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 በሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ ማጆ ቲቭት ኮሌጅ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/ሥ/ሂደት የጨረታ ሳጥን ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ የመጫረቻ ሰነዱን ሞልተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. ከቀኑ 6፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ ከቆየ በኋላ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በማጆ ቲቭት ኮሌጅ ግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/ሥ/ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡
7. 16ኛው /አስራ ስድስተኛው/ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
8. አሸናፊ ተጫራች ከኮሌጁ ጋር ውል ሲፈራረም ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የገንዘብ ዋስትና ለኮሌጁ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
9. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፋቸው ዕቃዎችን እስከ ማጆ ቲቭት (TVET) ቴከኒከና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ግቢ ድረስ በራሱ ወጭ አጓጉዞ የማስረከበ ግዴታ አለበት፡፡
10. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ማጆ ቲቭት (TVET) ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ
ስልክ፡- 0916370231/0927060625/0716193231
የማጆ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
