ብራይት ወርልድ ፎር ብላይንድ ውመን አሶሴሽን (Bright World for Blind Women Association)እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2025 የሥራ ዘመን የአንድ ዓመት የሂሳብ እንቅስቃሴውን በሙሉ በውጭ ኦዲተር ኦዲት ለማድረግ ይፈልጋል።
Bright World for Blind Women Association (ብራይት ወርልድ ፎር ብላይንድ ውመን አሶሴሽን)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ብራይት ወርልድ ፎር ብላይንድ ውመን አሶሴሽን (Bright World for Blind Women Association) የተባለ ሀገር በቀል ድርጅት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችና ኤጀንሲ ማስተዳደሪያ አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት ሰኔ 18/2011 ዓ.ም በመዝገብ ቁጥር 2906 በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ባለሥልጣን ተመዝግቦ ሕጋዊ ሰውነትን አግኝቷል።
ማኅበሩ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2025 የሥራ ዘመን የአንድ ዓመት የሂሳብ እንቅስቃሴውን በሙሉ በውጭ ኦዲተር ኦዲት ለማድረግ ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ አካላት ጨረታውን መወዳደር ይችላሉ።
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ የምዝገባ ፈቃድ እና 2 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሥራ ልምድ ያላቸው።
2. የታደሰ የንግድ ፈቃድና የግብር መለያ ሰርተፍኬት ያላቸው።
3. ሙያው በሚጠይቀው ጥራት በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰርቶ ማስረከብ የሚችሉ።
4. ግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን ጨረታው ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ የሚገልጽ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 5 ቀናት በማኅበሩ ቢሮ በመገኘት የሥራውን ስፋትና ዶክመንት በመመልከት የሥራውን ዋጋ በስም በታሸገ ፖስታ በድርጅቱ ቢሮ ማስገባት ትችላላችሁ።
ማኅበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት በታች የኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒኬሽን ቢሮ ከመድረሳችን በፊት የሚገኝ አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ እና ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የሚገኙበት ሕንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 409
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0910299325/0911607230 ደወለው መጠየቅ ይችላሉ።
ብራይት ወርልድ ፎር ብላይንድ ውመን አሶሴሽን
