በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤናና ጤ/ኅ/አ/ግ/ጥ/ቁ/ባለሥልጣን ባለኤሌክትሪክ ኤል ሞተር ሳይክል፣ የጽህፈት መሳሪያ እና ፅዳት ዕቃ ግዥ ከዚህ በታች በቀረበው መሰረት ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ በጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
የሲዳማ ክልል ጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶች እና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤናና ጤ/ኅ/አ/ግ/ጥ/ቁ/ባለሥልጣን ባለኤሌክትሪክ ኤል ሞተር ሳይክል፣ የጽህፈት መሳሪያ እና ፅዳት ዕቃ ግዥ ከዚህ በታች በቀረበው መሰረት ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ በጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት መጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. በዘርፉ ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታክስ ክሊራንስ፣ የቲን ተመዝጋቢና፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ለ15 /አሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ለዚህ ጉዳይ በተዘጋጀ ዝርዝር መግለጫዎች የያዘ ሰነድ (Specification) 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ መግዛት አለባቸው።
3. የጨረታ ሰነድ ላይ በመፈረም እና የድርጅታችሁን ማህተም በማስፈር ባለኤሌክትሪክ ኤል ሞተር ሳይከል ዋጋ በሰነድ ዋጋ መሙያ ፎርሙ ላይ በመሙላት ቫትን ያካተተና ያላካተተ ስለመሆኑ በመግለጽ፣ በማሳወቅ በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ በ16ኛው ቀን ከ6፡00 እስከ 8፡00 ሰዓት የጤናና ጤ/ነ/አ/ግ/ጥ/ቁ/ባለሥልጣን ግ/ክ/ን/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
4. ጨረታው 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 10፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ የዕረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ይከፈታል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር ብቻ/ CPO ወይም ኮንዲሽናል ፋይናንሻል የባንክ ዋስትና በማቅረብ መወዳደር አለባቸው።
6. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጊዜ በሁለት ኮፒ እና ኦርጅናል ፖስታ በማሸግ ቴክኒካ ፋይናንሻል የጨረታ ዶክመንት ለየብቻ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
7. የጨረታ ዋስና ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
8. የጨረታ ለ3 ወራት/90 ቀናት ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
9. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ግ/ክ/ን/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ሕንፃ 301 ክፍል 1 ማግኘት ይቻላል።
10. ባለስልጣን መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 046 212 3188
የሲዳማ ክልል ጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶች እና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን
