በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደብረ ማርቆስ ሪጅን ሰራተኞችን የስራ አልባሳት (ዩኒፎርም) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰፋት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደብረማርቆስ ሪጅን
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EEU/DMR/SPG/NCB-006/2018
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደብረ ማርቆስ ሪጅን ሰራተኞችን የስራ አልባሳት (ዩኒፎርም) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰፋት ይፈልጋል፡፡
በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
1. በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ታክስ ክሊራንስ መኖር አለበት፡፡
2. የጨረታ ሠነዱን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደብረማርቆስ ሪጅን ጽ/ቤት ደብረ ማርቆስ ቀበሌ 02 እምቦሳ የገበያ ማዕከል 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 13 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በካሽ በመክፈል ወይም በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት /EEU አካውንት ቁጥር 1000259834876 በማስገባት እና የባንክ ደረሰኝ በማምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦርጅናል በማለት እስከ ተጠቀሰው የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
5. ጨረታው ጥር 24 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ላይ ይከፈታል፡፡
6. ሪጅኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
7. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0581 78 46 33 / 0581 78 12 02 ወይም 09 44 26 54 45 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደብረማርቆስ ሪጅን
