Tender Detail

Tender Details

  • Company ጀምበር ሁለገብ የገ/ኀ/ማ/ዩንዬን ኃ.የተወሰነ
  • Address ሰሜን ወሎ ወልዲያ ከተማ ቀበሌ 06 : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0333310753
  • Website
  • Deadline29 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-29 00:00:00
  • Categories Cargo Vehicle

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ወልድያ ከተማ የሚገኘው ጀምበር ሁለ/የ/ህ/ስራ ማህበራት ዩንዬን (ኃላ.የተ) ለዩንዬኑ ምርት እና ግብዓት ለማጓጓዣ አገልግሎት የሚውሉ ሲኖ ካሶኒ 2025 ሞዴል ባለ 400 የፈረስ ጉልበት የጭነት ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ጀምበር ሁለገብ የገ/ኀ/ማ/ዩንዬን ኃ.የተወሰነ


ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ወልድያ ከተማ የሚገኘው ጀምበር ሁለ/የ/ህ/ስራ ማህበራት ዩንዬን (ኃላ.የተ) ለዩንዬኑ ምርት እና ግብዓት ለማጓጓዣ አገልግሎት የሚውሉ ሲኖ ካሶኒ 2025 ሞዴል ባለ 400 የፈረስ ጉልበት የጭነት ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1.     በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ደንበል ሲቲ ሴንተር ጀርባ በሚገኘው የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ቢሮ ቁጥር-103 የኢትዮጵያ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡

3.     የጨረታ ተሳታፊዎች የመሸጫ ዋጋቸውን በሰንጠረዥ በተገለፀው ዝርዝር ሁኔታ መሰረት መሙላት አለባቸው።

4.     የጨረታ ዋጋው ከመገለፁ በፊት የጨረታ ማስበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው።

5.     ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት አይቻልም፡፡

6.     በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡

7.     የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚጀመረው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ወይም 08/05/2018 ጀምሮ እስከ 21/05/2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

8.     ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 21/5/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡ በጨረታ መክፈቻ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ አከፋፈት ባይገኙም በጨረታ አከፋፈት ስርዓቱ ተገዥ ይሆናል ፡፡

9.     አሸናፊው እንደታወቀም አሸናፊው ያሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ ለውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ5 ቀን ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ዩንዬኑ የጨረታ ማስበሪያውን 2 በመቶ በመውረስ የራሱን አማራጭ ይወስዳል ።

10. ተጫራቾች ከጨረታው ጋር በተያያዘ እና ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎች በተዘጋጀው የተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተገዥ መሆን አለባቸው።

11. ዩንዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. ተጨማሪ ማብራሪያ ካለፈለገ በስልክ ቁጥር 0913692315/ 0947127956/0910452285/0333310753/ 0333311883 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 

አድራሻ፡- ሰሜን ወሎ ወልዲያ ከተማ ቀበሌ 06

ስልክ ቁጥር:- 0333310753/0333311883

ኢ-ሜይል:- alemnehbd7@gmail.com

 

ጀምበር ሁለገብ የገ/ኀ/ማ/ዩንዬን ኃ.የተወሰነ

Save Tender