Tender Detail

Tender Details

  • Company በደ/ምዕ/ኢ/ክ/መ/በካፋ ዞን የጌሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
  • Address ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline02 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-02 00:00:00
  • Categories Construction and Water Works , Building Construction , Finishing Work

በደ/ምዕ/ኢ/ክ/መ/በካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ የገነት ማዘጋጃ ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ ካፒታል በጀት በማዘጋጃ ቤቱ ግቢ ውስጥ የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ ተጀምሮ በመቋረጡ ያልተጠናቀቀውን እንዲጠናቀቅ እና ለቄራ አገልግሎት የሚሆነውን ለማሰራት ፈልጎ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ እንድናወዳድር ጠይቀውናል።

በደ/ምዕ/ኢ/ክ/መ/በካፋ ዞን የጌሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር ግ/009/18

በደ/ምዕ/ኢ/ክ/መ/በካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ የገነት ማዘጋጃ ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ ካፒታል በጀት በማዘጋጃ ቤቱ ግቢ ውስጥ የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ ተጀምሮ በመቋረጡ ያልተጠናቀቀውን እንዲጠናቀቅ እና ለቄራ አገልግሎት የሚሆነውን ለማሰራት ፈልጎ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ እንድናወዳድር ጠይቀውናል።

➢  በዚሁ መሰረት

የስራው ሁኔታና ቦታ ጌሻ ወረዳ የገነት ማዘጋጃ ቤት

•         ሎት 01 የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ማጠናቀቅ

•         ሎት 02. የቄራ አገልግሎት ግንባታ

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

✔  ደረጃ ዘጠኝ (9) እና ከዚያ በላይ የሆነ / B.C ወይም G.C/ ህጋዊ የግንባታ ፍቃድ ያለው።

✔  የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት፣ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፣

✔  የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ፣ ቫት ተመዝጋቢነት መረጃ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና ህጋዊ አቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

✔  ለመንግስት 3 በመቶ ታክስ ከሚያገኘው ገቢ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ፣

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለሃያ /20/ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጌሻ ወረዳ ገቢዎች ቅ/ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 34 ክፍል ተጫራቾች ለግንባታው የማይመለስ 300 ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ በመግዛት ቴክኒካል ኦርጅናል ብቻ ፣ ፋይናንሻል ዋናውንና ሁለት ኮፒውን ለየብቻ የግንባታውን ስም በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ የድርጅቱን ስም፣ ማህተምና ስልክ ቁጥር በመጻፍ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛ ቀን እስከ 3፡00 ሰዓት ድረስ በጌሻ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ስራ ሂደት የቢሮ ቁጥር 03 በመቅረብ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

1.       ተጫራቹ ድርጅቱ አሸናፊ መሆኑ ሲረጋገጥ ውል ሲገቡ የውል ማስከበሪያ 10% ለማስያዝ ፈቃደኛ የሆነ

2.       ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይናንስ ስራ ሂደት ቢሮ በ 21ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።

3.       ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት ጨረታውን አያስተጓጉልም።

4.       ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በሰንበት ወይም በበዓል ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ተላልፎ ጨረታው ይከፈታል።

5.       ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ለየብቻ ለሎት 01 9,000 ፣ ለሎት 02 10000 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6.       መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በደ/ምዕ/ኢ/ከ/መ/ በካፋ ዞን የጌሻ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት

Save Tender