ፐብሊክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን መስፈርቱን የሚያሟሉ ብቁ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 007/2018 ዓ.ም
ፐብሊክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን መስፈርቱን የሚያሟሉ ብቁ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት1፡ እቴንዳንስ ማሽን፤ ሎት 2 BSC Automation system ማልማት፤ ሎት3 ፕሪንተር እና ዲስከቶፕ ኮምፒተር፣ ሎት4 የጥበቃ አገልግሎት፣ ሎት5 የታፕሴሪ አገልግሎት፤ ሎት6 ደረቅ ኬክ 80 ግራም፤ ሎት7 ውሃ 330 ሊትር፣ ሎት 8 የተለያዩ ፕሪንተሮችና የፎቶ ኮፒ ማሽኖችን የጥገና ስራ የሚሰሩ፣ ሎት 9 የአውቶቢሶች ቦዲ ቀለም ብሉ ፔንት 426
1. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደርዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 በአካል በመምጣት ይችላሉ፡፡
2. ከሎት 1 እስከ ሎት 9 ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት በዘርፉ አግባብነት ያለው የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብርየከፈሉበትን እና የተጨማሪ እሴት ታከስ ሰርተፍኬት ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ከሎት 1 እስከ ሎት 9 ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የሚያቀርቡትን የጨረታ ሠነድ ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ሰነድ ኮፒ እና ኦርጅናል በሁለት ፖስታ በማዘጋጀትና በኤንቨሎፕ በማሸግ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ኃላፊነት በተሰጠው አካል ተፈርሞበት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
4. በሎት 6 ሎት 7 እና ሎት 9 ተጫራቾች ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ 2% ሲፒኦ /Bid Bond/ ወይም በባንከ የተመሰከረለት በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ላይተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 ይከፈታል። የጨረታ መከፈቻው ቀን የዕረፍት ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይከፈታል።
7. አገልግሎታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከሜከሲኮ ወደ ልደታ ቤተከርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ነው ለተጨማሪ መረጃ፡-ስልክ 011-5-50-45-64
የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት
