በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ቢሮው Electromechanical toolkit: DC voltmeter and soldering iron በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ቢሮው Electromechanical toolkit: DC voltmeter and soldering iron በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት በጨረታው ስመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
1. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምሰከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፊቃድ ያለው/ያላቸው/፣
3. በፋይናንስ መስሪያ ቤቶች በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ እና በህግ ያልተገደበ፣
4. ለእያንዳንዱ ዕቃ ግዥ በቢሮዉ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከቢሮው የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፣
5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የቴክኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናንሻል የጨረታ ሰነድን ለየብቻ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለእያንዳንዱ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው በየኤንቨሎፑ የውጭ ገጽ ዋና (ኦርጂናል) ወይም ኮፒ ብሎ በመፃፍና አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. በማንኛውም ኤንቨሎፕ ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ ማስገባት የለባቸው ምሳሌ ተጫራቾች የንግድ ፍቃድ፣ የቫት ሰነድ፣ መልካም አፈጻጸም ወዘተ መካተት ያለባቸው። በቴክኒክ የጨረታ ሰነድ በሆኑት በዋናው ኦሪጅናል እና ኮፒ ተብሎ በተገለጹት በሁለቱም ኤንቬሎፕ ሲሆን በፋይናንስ የጨረታ ሰነድ በዋናው /ኦሪጅናል/ ሆነ ኮፒ ኤንቬሎፕ ውስጥ ከፋይናንስ የጨረታ ሰነድ ውጭ ምንም ተጨማሪ መረጃ ማስገባት አይፈቀድም፤
7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ብቻ ሰነዱ የሚሽጥ ይሆናል። ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው በግልጽ ይከፈታል። ሆኖም 15ኛ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO የባንክ ጋራንቲ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
9. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
10. Electromechanical toolkit፡ DC voltmeter and soldering iron ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተያያዘና የተገለጸ በመሆኑ ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
አድራሻ፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወራቤ ቅርንጫፍ ህንፃ 1ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0467711180/0467710849 ይደውሉ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ
