Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462128588
  • Website
  • Deadline17 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-19 00:00:00
  • Categories Construction Machinery , Construction Vehicle

የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን ለ2018 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ የመንገድ ግንባታ ሥራ ለማሠራት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)


ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ የማሽን ኪራይ አገልግሎት ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 የግዥ መለያ ቁጥር፡ ሲ/መ/ባ/001/2018

 

የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን ለ2018 በጀት ዓመት በክልሉ ውስጥ የመንገድ ግንባታ ሥራ ለማሠራት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች መስፈርቱን ከሚያሟሉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

የማሽነሪ ዓይነት

ብዛት

ጠቅላላ ሰዓት

1

ግሬደር

15

12,750

2

ሮሌር

15

12,750

 

በዚሁ መሠረት፡-

1.     ተጫራቾች አግባብነት ያለውን ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውን የሚያሳይ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2.     ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር -5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።

3.     ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (Unconditional Bid) ከጠቅላላው ዋጋ 0.5% ሆኖ ከ500,000 ብር በላይ የሚበልጥ ከሆነ ብር - 500,000 ብቻ CPO ወይም ባንክ ጋራንት በማሰራት ለብቻው በማሸግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) 180 ቀን ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።

4.     የሚቀርቡ ማሽነሪዎች በሙሉ የፈረስ ጉልበታቸው፣ የስሪት ዘመናቸው እና ሌሎች መጫረቻ ሰነዱ ላይ የተገለጹ መስፈርቶችን የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

5.     የሚቀርቡ ማሽነሪዎች ወደ ሥራ በሚሰማሩበት ጊዜ እና ከአንዱ ፕሮጀክት ወደ ሌላ ፕሮጀክት ማሽነሪዎችን ማንቀሳቀስ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አሸናፊው ድርጅት በራሳቸው ወጪ አጓጉዘው ወጪው በባለስልጣኑ መ/ቤት የሚሸፈን ይሆናል።

6.     የሚቀርቡ ማሽነሪዎች የኢንጂን ሰዓታቸው እና የነዳጅ አዲዮሜትር በትክክል የሚሰራ መሆን አለበት።

7.     ከዚህ በፊት ከሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን ጋር ውለታ ገብቶ በአፈፃፀም ችግር ምክንያት ማስጠንቀቂያ ተሰቶት ማሸነሪዎችን ወደ ሥራ ያላስገባና ውላቸው የተቋረጠ የማሽነሪ አከራይ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም።

8.     የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ የጨረታ ማስከበሪያ /Bid Security/፣ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒ ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት። ከላይ የተጠቀሰዉ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የእረፍት ወይም የሕዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።

9.     በጨረታ ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ሕጎች አለማክበር በመጫረቻ ሰነዶቻቸው በሁሉም ገጽ ላይ ማህተምና ፊርማ ያለማድረግ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ያለበት የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በባለስልጣኑ መ/ቤት አደራሽ ይከፈታል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0462-128-446

 

የሲዳማ ክልል መንገዶች ባለስልጣን

Save Tender