Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
  • Address አማራ ክልል: ኢትዮጵያ, Phone: 033-4-40-12-30
  • Website
  • Deadline22 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-22 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Electronics Materials , Machinery Spare Parts , Construction Works

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለብሔረሰብ አስተዳደሩ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸውን የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የከባድ ማሽን መለዋወጫ አቅርቦትና የግንባታ ስራ ግዥን በሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ


የደንብ ልብስ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የከባድ ማሽን መለዋወጫ አቅርቦትና

የግንባታ ሥራ ግዥ ሃገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ለብሔረሰብ አስተዳደሩ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸውን የሰራተኞች ደንብ ልብስ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የከባድ ማሽን መለዋወጫ አቅርቦትና የግንባታ ስራ ግዥን በሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1.     ከሚወዳደሩት አቅርቦት ወይንም አገልግሎት ግዥ ጋር የተዛመደ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የተሰጣቸው ፈቃድ አንድ አመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።

2.     ለምክር ቤት አዳራሽ ጥገና ሥራ እና አስተዳደር ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሚሰራው መፀዳጃ ቤት ደረጃ ሠባትና ከዛ በላይ ጠቅላላ ሥራ ተቋጭ እንዲሁም ጤና መምሪያ ሊያሰራ ለፈለገው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ ሥራ ደረጃ አምስትና ከዛ በላይ ሥራ ተቋራጭነት የንግድ ፍቃድና የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።

3.     የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት (Tax Payer identificatin Number) ያላቸው።

4.     የተጨማሪ እሴት ታክስ (value Added Tax Certificate) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

5.     ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

6.     የሚገዙትን እቃና የግንባታ ሥራ ዝርዝር መግለጫ (Specification) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።

7.     ተጫራቾች ለደንብ ልብስ፣ ለኤሌክትሮኒክስና ለከባድ ማሽን መለዋወጫ እቃዎቹ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) እና ለግንባታ ሥራዎቹ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ፡፡

8.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለደንብ ልብስ፣ ለኤሌክትሮኒከስና ለከባድ ማሽን መለዋወጫ እቃዎቹ ከጠቅላላ ዋጋው 1% (አንድ በመቶ) እንዲሁም ለግንባታ ሥራዎቹ ከጠቅላላ ዋጋው 2% (ሁለት በመቶ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (የማይሻርና ያለተጨማሪ ስነ-ስርአት በመጠየቅ ብቻ ተከፋይ የሚሆን የባንክ ዋስትና) ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ዋናውን የገቢ ደረሰኝ /ማስያዝ አለባቸው።

9.     ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን አንስቶ ለእቃ አቅርቦቶቹ እስከ ተከታታይ አስራ አምስተኛው ቀን ለግንባታሥራዎቹ እስከ ተከታታይ ሃያ አንደኛው ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ሠነዱን በመግዛት የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በዋ/ኸ/ብ/አስ/ር/M/መምሪያ ግ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለእቃ አቅርቦቶቹ እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን ለግንባታ ሥራዎቹ እስከ ሃያ ሁለተኛው ቀን 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋ/ኸ/ብ/አስ/ር/ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 ጨረታ በጋዜጣ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ የእቃ አቅርቦቶቹ በአስራ ስድስተኛው ቀን የግንባታ ሥራዎቹ በሃያ ሁለተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡01 ታሽጎ ከጠዋቱ 3፡30 የሚኪፈት ሆኖ ለጤና መምሪያ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ ሥራ ከቴክኒካል ውጤቱ ሠባ በመቶ በላይ ያመጡ ተጫራቾች ለዋጋ ውድድሩ የሚያልፉ ይሆናል፡፡ ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰአት ከመንግሥት የስራ ቀን ውጭ ከሆነ በተመሣሣይ ሰዓት በሚቀጥለው የመንግስት የስራ ቀን ይከፈታል።

11. መምሪያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነት የማይወስድ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

12. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በዋ/ኸ/ብ/አስ/ር /ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ር/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በአካል በመገኘት ወይንም በስልክ ቁጥር 0334401230/0249/0062 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

Save Tender