Tender Detail

Tender Details

  • Company የሐሴት ጅምላ ንግድ ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር
  • Address አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 07 ገብርኤል ቤተከርስቲያን ጀርባ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251114403103
  • Website
  • Deadline15 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-15 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing

የሐሴት የጅምላ ንግድ ቢዝነስ አክሲዮን ማኅበር በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ እና አግባብነት ባላቸው የፋይናንስ ደንቦች መሠረት፤ ለቀጣዮቹ ሦስት ተከታታይ ዓመታት (ከ2018 ዓ.ም እስከ 2020 ዓ.ም) የድርጅቱን ዓመታዊ የሂሳብ መዛግብት የሚመረምር እና የኦዲት ሪፖርት የሚያቀርብ ሕጋዊ ፈቃድ ያለው የውጭ ኦዲተር በጨረታ አወዳድሮ መሾም ይፈልጋል።

የሐሴት ጅምላ ንግድ ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር


የውጭ ኦዲተር ቅጥር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የሐሴት የጅምላ ንግድ ቢዝነስ አክሲዮን ማኅበር በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ እና አግባብነት ባላቸው የፋይናንስ ደንቦች መሠረት፤ ለቀጣዮቹ ሦስት ተከታታይ ዓመታት (ከ2018 ዓ.ም እስከ 2020 ዓ.ም) የድርጅቱን ዓመታዊ የሂሳብ መዛግብት የሚመረምር እና የኦዲት ሪፖርት የሚያቀርብ ሕጋዊ ፈቃድ ያለው የውጭ ኦዲተር በጨረታ አወዳድሮ መሾም ይፈልጋል።

ተፈላጊ መስፈርቶች፡-

1.     በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ (AABE) የተሰጠ የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

2.     የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው።

3.     የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

4.     በዘርፉ በተለይም በአክሲዮን ማኅበራት እና በጅምላ ንግድ ኦዲት ሥራ ላይ በቂ ልምድ ያለው፡፡

የመወዳደሪያ ሰነድ አወሳሰድ፡-

ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘውን የመወዳደሪያ ሰነድ የማይመለስ 300.00 (ሦስት መቶ) ብር በመክፈል አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 7፣ ቃሊቲ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በአስተዳደርና ፋይናንስ ክፍል በመገኘት መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

የአቀራረብ ሁኔታ፡-

ተጫራቾች የቴክኒክ እና የፋይናንስ ፕሮፖዛላችሁን በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በአካል በመቅረብ ማስገባት ይኖርባችኋል።

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ስልክ:- 0114-403103/0930000129

ማኅበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የሐሴት የጅምላ ንግድ ቢዝነስ አክሲዮን ማኅበር

Save Tender