በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን ሣንኩራ ወረዳ ፋይናንስ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በስልጤ ዞን የሣንኩራ ወረዳ ፋይናንስ/ጽ/ቤት
ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን ሣንኩራ ወረዳ ፋይናንስ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ጨረታውን መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርቶች መሰረት መወዳደር የሚችል ይሆናል።
1. ፒክ አፕ ደብል ጋቢና መኪና እና ባጃጅ
2. የተለያዩ ሞተር ተሽከርካሪዎች እና ሳይክሎችን
3. የተለያዩ የመኪና ጎማዎችን
4. የተለያዩ የእርሻ መሳሪያዎችን እና ለግንባታ ሥራ የሚውሉ እቃዎችን
5. ጀኔሬተር
6. የተለያዩ ብረታ ብረቶችን
7. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን
የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት1፡- 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/፣ ከሎት2 እስከ 7 ድረስ ብር 5,000 በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል።
የጨረታ ሠነዱን በሳንኩራ ወረዳ ፋይናንስ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 ለእያንዳንዱ ስነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መግዛት የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሠነዱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጂናል 01 ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የሥራ ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ በወረዳዉ ፋይናንስ ፅ/ቤት በተዘጋጀዉ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥን በዚሁ ዕለት ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ታሽጎ ካቀኑ 8፡00 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡- እቃወቹን መመልከት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት እለት ድረስ መመልከት የሚቻል መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡
ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ሣንኩራ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስልክ 046 237 0081/0913 743 709/ 0913 06 77 49/0910 044 175
በስልጤ ዞን የሣንኩራ ወረዳ ፋይናንስ/ጽ/ቤት
