Tender Detail

Tender Details

  • Company Lihiket Design & Supervision Corporation Bahir Dar (የልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ባህርዳር)
  • Address አፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ ባህርዳር ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 058-218-02-73
  • Websitehttps://lihiket.com/
  • Deadline20 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-20 00:00:00
  • Categories Computer Laptop And Accessories , Office Machines And Computers , Materials

ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ፕቶፕ ኮምፒውተሮች እና ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች እና ሌሎች ተዛማጅ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Lihiket Design & Supervision Corporation Bahir Dar (የልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ባህርዳር)


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ማለትም፡-

–       ላፕቶፕ ኮምፒውተር ብዛት 67

–       ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ብዛት 04 እና ሌሎች ተዛማጅ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት በማሟላት በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡

1.     በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

2.     ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ባህር ዳር በግዥና ንብ/አስ/ቡድን የሥራ ክፍል በሮ ቁጥር 08 በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀን ድረስ መግዛት ይቻላል፡፡

3.     ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8፡30 ሰዓት ላይ ለመገኘት የቻሉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡

4.     ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን፣ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በሲ.ፒ.ኦ ወይም እንደተጠየቀ ወዲያውኑ በሚከፈል የባንክ ጋራንቲ በፖስታ አሽገው እስከ ጨረታ መዝጊያው ቀንና ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 08 ማቅረብ ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡

5.     ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 058-218-02-73 ሞባይል 0918-08-55-89

/09-96-14-20-56 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 058-218-05-50 በመላክ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን

Save Tender