የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 003/18
የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቶች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ አዲስ አባባ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ክፍል በመክፈል ደረሰኝ ይዘው ቢሮ ቁጥር 208 ከእቅርቦትና ኮንትራት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ንብረቶችን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የዝዙበትን ደረሰኝ በመያዝ አዲስ አበባ ዋና ግቢ እና ደብረዘይት ሥልጠና ማዕከል በመገኘት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የጨረታ ሰነድ ላይ የተገለፀውን ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውል እና በ15ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
- የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው፡፡
- ኢንስቲትዩቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ በመክፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኢንስቲትዩቱ ገቢ ይደረጋል።
- ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንደአስፈላጊነቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09
ስልክ ቁጥር ፡- 0116-454147/0116-453598 /0118-694931 ከሰዓሊተ ምህረት ማርያም ቤ/ከርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘው ሕንፃ
የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት
