በመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የሜ/ጄ ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ያገለገሉ የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር በሕብረት ትምህርና ሥልጠና ዋና መምሪያ የሜ/ጄ ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴ/ኮሌጅ
የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች የጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር ግ/001/2018 ዓ/ም
በመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የሜ/ጄ ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ያገለገሉ የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ የሆነ የታደሰ መታወቂያ ያለው መሆን ይጠበቅባችኋል።
ለሽያጭ የቀርበ የዕቃው ዓይነት
- የተለያዩ የህክምና ኪቶች፣ የተለያዩ ኦክስጅን ሲሊንደሮች፣ የተለያዩ የፕሪንተር ቀለም ካርትሬጆች፣ የተለያዩ የተጓደሉ የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች፣ የተለያዩ ላፕቶፖች፣ ኮምፒውተርና አክሰሰሪዎች፣ የተለያዩ የተጓደሉ አነስተኛ ጄኔሬተሮች እና ሌሎች በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፁ ያገለገሉ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች -
- የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሠረት ይሆናል።
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ በፋይናንስ ዴስክ በኩል በመክፈል የከፈሉበትን ደረሰኝ ይዘው ሰነዱን ከግዥ ዴስክ መግዛት ይቻላል።
- የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎች የያዘውን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገባት አለበት።
- የጨረታ መክፈቻ በ05/05/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ መሰብሰቢያ አዳራሽ በይፋ ይከፈታል፤
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0112371140 ወይም ፋክስ ቁጥር 0112371818
አድራሻ፡- ሜ/ጄ ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴ/ኮሌጅ ሆለታ ገነት
የሜ/ጄ ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
