የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት የዲጂታል ሜትር የታክሲ አገልግሎት አቅራቢ እና አስተዳደር ድርጅቶችን አወዳድሮ በረጅም ጊዜ ውል ለማሰራት ይፈልጋል።
Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
በድጋሜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር SSNT-T594
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት የዲጂታል ሜትር የታክሲ አገልግሎት አቅራቢ እና አስተዳደር ድርጅቶችን አወዳድሮ በረጅም ጊዜ ውል ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆነ ተጫራች በተጠቀሰው አገልግሎት ዘርፍ ላይ ቢያንስ ሁለት (2) ዓመት የሰራ ፣ በሶፍትዌር ልማት (ዲዛይን፤ ማበልፀግ እና አተገባበርን ጨምሮ) የጥሪ ማዕከል አገልግሎት ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የሙያ ብቃት የምስክር ወረቀት ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ እና በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ የሚያገለግል ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ TIN (የግብር መለያ ቁጥር) ያለውና በዘርፉ እየሰራ ያለ ማንኛውም ተቋም በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T594 በሚል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጂውን (Deposit Slip Copy)፣ የጨረታውን ቁጥርና አይነት እንዲሁም የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
የጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው ባንክ ጋራንቲ (unconditional bank guarantee) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም። አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል። ተጫራቾች በጨረታው ሠነድ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ የስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እሰከ ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ፕሮኪውርመንት እና ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት ክፍል
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
በስልክ ቁጥር 011 517 8025
ኢ-ሜይል: eskedarya@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው፡፡
