በአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሰሜን ጤና ጣቢያ ለ 2018 በጀት ዓመት ልዩ ልዩ የጽዳት ዕቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ቋሚ የህክምና መሣሪያዎች፣ የህትመት ውጤቶች መድሐኒት እና የላቦራቶሪ ሪኤጀንቶች፣ እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ፣ ዕቃዎች እና መገልገያ መሣሪያዎች፣ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሰሜን ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 02/2018
በአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ሰሜን ጤና ጣቢያ ለ 2018 በጀት ዓመት ልዩ ልዩ የጽዳት ዕቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ቋሚ የህክምና መሣሪያዎች፣ የህትመት ውጤቶች መድሐኒት እና የላቦራቶሪ ሪኤጀንቶች፣ እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና መገልገያ መሣሪያዎች፣ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ፡-
- የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ፣ በመድኃኒት፣ የላቦራቶሪ ሪኤጀንት እና የህክምና መገልገያ መሣሪያ ለሚሳተፉ የመድኃኒት አቅራቢ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ እና ለሁሉም ፣ በአቅራቢ፣ ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት (በስራ ሰዓት) በጤና ጣቢያው 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 በሚገኘው ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ከ ፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለየምድቡ (ሎት) የተመደበውን የብር መጠን በCPO ማስያዝ አለባቸው። ከአንድ በላይ በሆነ ሎት የሚሳተፉ ተጫራቾች ለየሎቱ የተመደበውን የብር መጠን ድምር በ CPO ማስያዘ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሰነዶች እና የሞሉትን ዋጋ ዋና እና ኮፒ በፖስታ በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ በወጣ እስከ 11ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ድረስ (በስራ ሰዓት) በጤና ጣቢያው 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታው ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚው ዕለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ማቅረብ ያለባቸው ከጤና ጣቢያው በሚወስዱት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ብቻ ነው።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው። የህትመት ውጤቶች ጤና ጣቢያው በሚያቀርበው ናሙና መሰረት የሚዘጋጁ ይሆናል፡፡
- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ስሙ ሰሜን ማዘጋጃ ስልክ ቁጥር 0111-12 94 72
በአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የሰሜን ጤና ጣቢያ
