በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ-8 ፋይናንስ ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ፣ የደንብ ልብስ፣ የጽዳት እቃዎችን፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የኤሌክትሮኒክስ እና ሌሎች የቢሮ መገልገያ ጥገና አገልግሎቶች፣ የመስተንግዶ አገልግሎት፣ የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት እና የሞንታርቦ፤ ድንኳን፤ ጀኔሬተር አና ሌሎች ኪራይ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ-8 ፋይናንስ ጽ/ቤት
የ2ኛ ዙር ብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር: ጉ/ክ/ከ/ወ8/002/2018
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ-8 ፋይናንስ ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ፣ የደንብ ልብስ፣ የጽዳት እቃዎችን፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የኤሌክትሮኒክስ እና ሌሎች የቢሮ መገልገያ ጥገና አገልግሎቶች፣ የመስተንግዶ አገልግሎት፣ የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት እና የሞንታርቦ፤ ድንኳን፤ ጀኔሬተር አና ሌሎች ኪራይ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተለውን መሰፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት እና ቲን ነምበር ያላቸው መሆን አለባቸው።
- Tot 3%፤ እና 10% ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ መወዳደር ይችላሉ
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ወይም በአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ያቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ለሚጫረቱባቸው እቃዎች እንዳስፈላጊነቱ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- የታደሰ ንግድ ፋቃድ እና የንግድ ፍቃድ የምስክር ወረቀት ያላቸው በተሰጠበት የንግድ ዘርፍ ብቻ መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበሪያ በጽ/ቤቱ ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከአንድ ሎት በላይ የሚወዳደሩ ከሆነ የጨረታ ማሰከበሪያውን በተናጠል ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
|
ሎት ቁጥር
|
አላቂ የጽህፈት መሳሪያ
|
የተጠየቀዉ የጨረታ ማስከበሪያ (በኢትዮጵያ ብር)
|
|
1
|
አላቂ የጽህፈት መሳሪያ
|
12,216
|
|
2
|
የፅዳት ዕቃዎች
|
17,973
|
|
3
|
የደንብ ልብስ
|
21,750
|
|
4
|
ቋሚ የቢሮ እቃዎች
|
20,000
|
|
5
|
የትራንስፖርት አገልግሎት
|
5,000
|
- በጨረታው ያላሸነፉ ድርጅቶ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለሰላቸዋል።
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚውል ሲሆን ብር 500.0 (አምስት መቶ ብር) የኢትዮጵያ ብር በመክፍል የጨረታ ሰነዱ ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ-8 ፋ/ኢ/ል ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 መውሰድ ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በማሽግ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸው
- በአምራች ዘርፍ የተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ብቻ የተደራጁ አካላት መወዳደር መወዳደር ይችላሉ። ከፈለጉ በጽ/ቤት ኃላፊ የተፈረመ የዋስትና ደብዳቤ ማስረጃ ሲያቀርቡ የጨረታ ሰነድ ወስደው መወዳደር ይችላሉ።
- በአምራች ዘርፍ የተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው ማስረጃ በማቅረብ የሚወዳደሩ ድርጅቶች ለውል ማስከበሪያ የሚሆን በጽ/ቤት ኃላፊ የተፈረመ የዋስትና ደብዳቤ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ-8 ፋ ኢ/ል ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በ10ኛው ቀን በ10፡00 ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- አንዱ በአንዱ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- ተጫራቾች የአንዱ ነጠላ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መጠቀስ አለበት። ያልተጠቀሰ ከሆነ ቫት እንዳካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
- አሸናፊው ያሸነፈባቸዉን ንብረቶች የወረዳው ንብረት ክፍል ድረስ ገቢ ማድረግ አለበት (የሰራተኛ እና የትራንስፖርት ወጪ አቅራቢ ድርጅቱ የሚችል ይሆናል) ።
- አድራሻችን ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ-8 አስተዳደር አዲሱ ገቢያ ጤና ጣቢያ በስተጀርባ ነው።
- ፖስታዎቹ መታሸግና በላያቸው ላይ ማህተም መደረግ ይኖርባቸዋል።
- መስሪያ ቤቱ በጨረታ በተገለፀው የዕቃ መጠን ላይ 20% የመጨመር ወይንም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው
- መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ-8 ፋ/ኢ/ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2
ለበለጠ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 0111547450 መደወል ይችላሉ።
ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ-8 ፋይናንስ ጽ/ቤት
