Tender Detail

Tender Details

  • Company በዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽ የምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት
  • Address ደሴ ካራ ጉቱ ግብርና ፊት ለፊት ከሚገኘው ምስ/አማ/ማስ/ጽ/ቤት፣ አ.አ ለገሀር አመልድ ህንፃ 7ኛ ፎቅ ዘመን አ.አ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0331124973
  • Website
  • Deadline17 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ፐርሰንት/
  • opening date2026-01-17 00:00:00
  • Categories Building Materials , Construction Materials And Raw Materials , Sanitary Ware

በዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት ስር ለሚገኙ ፕሮጀክቶች ማለትም ለግዳን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፤ ለአሚኮ ቢሮ ግንባታ ፕ/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የግንባታ ማጠናቀቂያ እቃዎች እና የሳንተሪ እቃዎች አቅርቦት እንዲሁም የገጠማ ስራዎችን ህጋዊና ብቃት ካላቸው አቅራቢዎች በሎትና በነጠላ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

በዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽ የምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት ስር ለሚገኙ ፕሮጀክቶች ማለትም ለግዳን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፤ ለአሚኮ ቢሮ ግንባታ ፕ/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የግንባታ ማጠናቀቂያ እቃዎች እና የሳንተሪ እቃዎች አቅርቦት እንዲሁም የገጠማ ስራዎችን ህጋዊና ብቃት ካላቸው አቅራቢዎች በሎትና በነጠላ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ፡-

  1. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት እቃ ዘርፍ ላይ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የማንኛውም የግዥ መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ከፋይነት የተዘገቡ /መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ ከብር 20 ሺህ በላይ ለሆነ ግዥ የቫት 15% ማማሹን /50%/ እና ከተከፋይ ሂሳብ ላይ 3% ዊዝ ሆልዲንግ ታክስ ይቆረጣል።
  2. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የአገልግሎት ዓይነት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በዘመን የምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት በደሴ ከተማ በአስተዳደርና ፋይናንስ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 16 እና ዘመን አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ለአንድ የጨረታ ሰነድ በብር 300.00 መግዛት ይችላሉ።
  3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት አልቆ በ16ኛው ቀን በዘመን ምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት/ደሴ ከተማ/ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ይከፈታል፤ ተጫራቾች በእለቱ ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል። ያልተገኘ ተጫራችም በጨረታ ሂደቱ ተገዥ ይሆናል፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደሩበትን የእቃ ዓይነት ስፔስፊኬሽን አይቶ በትክክል ዋጋ በመሙላት የሚጫረቱበትን ዋጋ በአንድ ወይም ወጥ በሆነ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማዘጋጀት በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ ደሴ ከተማ በሚገኘው በዘመን ምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት ግዥ ኦፊሰር ቢሮ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ከማሸጊያው ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ማንኛውም ተጫራቾች ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ፐርሰንት/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /cpo/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
  7. አሸናፊው ሲታወቅ ላሸነፈው እቃ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /በcpo/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ያሸነፈውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት መጫኛና ማውረጃ እና የቴስት ማሰሪያ ወጭን ጨምሮ ተጫራቹ ችሎ የእቃውን ጥራት በአማካሪ በማረጋገጥ እና ቴስት ለሚያስፈልጋቸው ግብአቶች ቴስት በማሰራት ማለፉ በአማካሪ በማረጋገጥ ያሸነፈውን እቃ ፕሮጀክቱ በሚገኙበት መጋዘን ድረስ ገቢ ማድረግ ግዴታ ነው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ማቅረብ እንዳለበት ተገንዝቦ ዋጋ መሙላትና መወዳደር ያለበት ሆኖ የሚሞላው የ 1 ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በሚሸጠው ጨረታ ሰነድ ዋጋ መሙያ ፎርም መሰረት ቫትን ያካተተ መሆን ሲገባው በእስክርቢቶ ቫት ይጨመርበት ተብሎ ከተጻፈ ተጫራቹ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
  9. በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ እንዳይኖር በጥንቃቄ ይሞላ፡፡ በአጋጣሚ ስርዝ ድልዝ ከተፈጠረም ፓራፍ ይደረግ፡፡ ተጫራቾች እኩል ዋጋ በሚያቀርቡበት ጊዜ 1ኛ ብዛት ላሸነፈው ቅድሚያ ይሰጣል እንደዛም ሆኖ እኩል ከሆኑ በእለቱ በተገኙት ተጫራቾች ፊት በእጣ ይለያል፡፡ ተጫራቾች ካልተገኘም እጣው በኮሚቴው ይጣላል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ሆኖ ተጫራቹ በዚህ ምክንያት ለሚያወጣው ወጪ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስ.ቁ. 0331124973/0333111009 ወይም 0111265652 አ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ይጠይቁ።

 

አድራሻ፡-  ደሴ ካራ ጉቱ ግብርና ፊት ለፊት ከሚገኘው ምስ/አማ/ማስ/ጽ/ቤት፣ አ.አ ለገሀር አመልድ ህንፃ 7ኛ ፎቅ ዘመን አ.አ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት

 

በዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽ የምስራቅ አማራ ማስ/ጽ/ቤት

 

Save Tender