በ2018 ዓ.ም ሀዋሳ ዱቄትና ዳቦ ኢንተርፕራይዝ በግዥ መለያ ቁጥር ሀ/ዱ/ዳ/ኢ/002097/2018 ጥራት ያለው ለዳቦ ምርት የሚሆን ስንዴ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ዱቄትና ዳቦ ኢንተርኘራይዝ
የጨረታ ማስታወቂያ
በ2018 ዓ.ም ሀዋሳ ዱቄትና ዳቦ ኢንተርፕራይዝ በግዥ መለያ ቁጥር ሀ/ዱ/ዳ/ኢ/002097/2018 ጥራት ያለው ለዳቦ ምርት የሚሆን ስንዴ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ፣ ከፌዴራል ሀገርውስጥ ገቢ ወይንም ከሌሎች ግብር ሰብሳብቢ የመንግስት መ/ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በመንግስት ጨረታዎች መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond/Security) 50,000 ሃምሳ ሺህ ብር በባንክበተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO የጨረታው ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
3. በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500 አምስት መቶ ብር በመከፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከሀዋሳ ዱቄትና ዳቦ ኢንተርፕራዝ በሚገኘው ማምረቻ ግቢ ቢሮ ቁጥር 01 አስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ ከፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ከቀኑ 11:00 ሰዓት ዘርፍ ከፍል በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው ሀዋሳ ዱቄትና ዳቦ ኢንተርፕራይዝ ማምረቻ ግቢ በሚገኘው የመዝናኛ ከበብ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8:30 ላይ ይከፈታል። ሆኖም ዕለቱ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም አገር አቀፍ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
5. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ዱቄትና ዳቦ ኢንተርኘራይዝ
