በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ከአ.አ 90 ኪ/ሜትር ርቀት ከሚገኘው ዋናው ሙገር ፋብሪካ አሮጌ ጎማዎች፣ አሮጌ ባትሪ እና ቁርጥራጭ ብረታ ብረት በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የከባድ መኪና፣ የትናንሽ መኪና እና የማሽነሪ አሮጌ ጎማዎች፣ አሮጌ የመኪና ባትሪ እና ቁርጥራጭ ብረታ ብረት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ከአ.አ 90 ኪ/ሜትር ርቀት ከሚገኘው ዋናው ሙገር ፋብሪካ አሮጌ ጎማዎች፣ አሮጌ ባትሪ እና ቁርጥራጭ ብረታ ብረት በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን አሟልተው መወዳደር ይችላሉ፣
1ኛ/ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይም የግብር ከፋይ መለያ /ቲን/ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
2ኛ/ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከመጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀን ባሉት ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ተእታክስን ጨምሮ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ/ በመክፈል የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ሰነድ አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ በሚገኘው ጋራድ ሕንፃ ማርኬቲንግ ቢሮ መግዛት ይኖርባቸዋል ፤
4ኛ/ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 4% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
5ኛ/ ተጫራቾቸ ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች በሚገኙበት መግር ዋና ፋብሪካ በመቅረብ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማየት ይችላሉ፡፡
6ኛ/ ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀን ድረስ የሚገዙበትን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመሙላትና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይንም የግብር ከፋይ መለያ/ቲን ኮፒ ከጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎኘ ውስጥ በማድረግ አዲስ አበባ ጋራድ ሕንፃ በሚገኘው የማርኬቲንግ መምሪያ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ብቻ ማስገባት አለባቸው።
7ኛ/ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በማርኬቲንግ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡
8ኛ) ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ
አዲስ አበባ በቅሎ ቤት ጋራድ ሕንፃ በሚገኘው የማርኬቲንግ መምረያ ቢሮ በመቅረብ ወይም 0114 40 30 26/0114-40-3025 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
