Tender Detail

Tender Details


በአማራ ክልል በሰሜን ሽዋ ዞን በሚዳ ወረሞ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለተቋሙ አገልግሎት የሚውል ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ገኛ የፅህፈት መሳሪያዎች 2ኛ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች 3ኛ የህትመት ስራዎች 4ኛ የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች 5ኛ የፅዳት እቃዎች 6ኛ ፍራሽና ብርድልብስ 7ኛ የተለያዩ ቋሚ እቃዎች 8ኛ የውሃ እቃዎች 9ኛ የፕሪንተር ቀለም 10ኛ የግንባታ እቃዎች ከኛ ፈርኒቸር 12ኛ የመኪና ጎማ 13ኛ አልሙኒየም እና አከሰሰሪ 14ኛ መስታወት 15ኛ የታፔላ ሥራ ከነማቴሪያሉ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የሚዳ ወረሞ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ክልል በሰሜን ሽዋ ዞን በሚዳ ወረሞ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለተቋሙ አገልግሎት የሚውል ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን 1ኛ የፅህፈት መሳሪያዎች 2ኛ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች 3ኛ የህትመት ስራዎች 4ኛ የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች 5ኛ የፅዳት እቃዎች 6ኛ ፍራሽና ብርድልብስ 7ኛ የተለያዩ ቋሚ እቃዎች 8ኛ የውሃ እቃዎች 9ኛ የፕሪንተር ቀለም 10ኛ የግንባታ እቃዎች ከኛ ፈርኒቸር 12ኛ የመኪና ጎማ 13ኛ አልሙኒየም እና አከሰሰሪ 14ኛ መስታወት 15ኛ የታፔላ ሥራ ከነማቴሪያሉ በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

1. በ2018ዓ.ም በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብርከፋይነት መለያ ቁጥር/ቲን/እንዲሁም በጨረታ ሰነድ ላይ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ድምር ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቀናት ለዕቃ አቅርቦት እስከ 15 ቀን ከቀኑ 11፡30 ስዓት ድረስ የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በሚዳ ወረሞ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን በመገኘት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የነጠላ እና የጠቅላላ ዋጋ በዝርዝርተሞልተው ኮፒ እና ኦርጅናል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ባንኮች የሚሰጥ 2% ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይንም በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት በጥሬ ገንዘብ ወይም በገቢ ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ከማንኛውም ከተፈቀደለት ባንከ የሚቀርብ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ C.P. O በአማርኛ ተተርጉሞ በአባሪነት ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች በአዲሱ የንግድ ስራ መስጫ መደብ እና የተሰማሩበት የንግድ ስራ ፍቃድ መስጫ ኮድ ቁጥር፣ የንግድ ስራ ፍቃድ መስጫ መደብ እና የተሰማሩበት የስራ መስኮች በተገለፀው ትንታኔ የተፃፈው ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡

6. ተጫራቾች የዕቃውን ዋጋ በዝርዝርና በጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስም፣ ፊርማና ማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ 16ኛ ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ በሚዳ ወረሞ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በግ/ፋ/ን/አስ _ ቡድን ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. የጨረታው ተጫራቾች በአካልም ሆነ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በሚዳ ወረሞ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡

8. የጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ዕቃውን በሚዳ ወረሞ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በሚገኘው ንብረት ክፍል ግቢ ውስጥ ማድረስ ይኖርባቸዋል፡፡

9. ተጫራቾች በተቀመጠላቸው ከፍት ቦታ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖር ሞዴል፣ ብራንድ/መለያ/ የተመረተበትን ሀገር በሚነበብ ፅሁፍ (ግልጽ በሆነ ፅሁፍ) አካቶ በትከከል መሙላት አለበት፡፡

10. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ጥራት ያለውና ኦርጅናል እቃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን፡- 0926799107 / 0913684697 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን የሚዳ ወረሞ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

Save Tender